ባራክ ኦባማ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዓተ ቀብር የሚገኝ ቡድን እንደሚልኩ አስታወቁ

አዲስ አበባ ነሃሴ 25/2004 የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዓተ ቀብር ላይ የሚገኝ የልዑካን ቡድን ዛሬ ይፋ አደረጉ። በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የፕሬዝዳንቱ ልዑካን በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ ቋሚ ተወካይ በአምባሳደር ሱዛን ራይስ መሪነት ነሐሴ 27 ቀን 2004 ዓ.ም በሚፈጸመው ሥርዓተ ቀብር ላይ ይገኛል። የፕሬዝዳንቱ ልዑካን አባላትም በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ፣ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሃፊ ጆኒ ካርሰን እና የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪና የብሔራዊ ደህንነት ከፍተኛ ዳይሬክተር ሚስ ጋይሌ ስሚዝ ናቸው።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር