የሲዳማ ዞን ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መመሪያ፣ የእዥ ወረደ አስተዳደር በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀዋል፡፡

ክቡር ጠቀላይ ሚኒስትር የሴቶችንና የወጣቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን እንዲሁም የህፃናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ ምቹ የሆኑ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን በመንደፍና ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡
በርሳቸው አመራር ኃላ ቀርነትን ታሪክ ለማድረግና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል መሠረት ተጥሏል፡፡ ይሁን እንጂ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ሞት የከፋ ሀዘን ተሰምቶናል ብለዋል፡፡
 

በተመሳሳይ የሀዋሳ እርሻ ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ መፅሐፍ ቅዱስ ማህበር ሀዋሣ ቅርንጫፍ ሀገራችንን በበሳል አመራር ላለፉት 21 አመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በመምራትና ትክክለኛ የእድገት መንገድ በመቀየስ መሪ ሚና የተጫወቱት ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰትር በመለየታቸው ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው አመልክተዋል፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/21NehTextN204.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር