የሲዳማ ዞን ግብርና መምሪያ አመራሮችና ሠራተኞችን ጨምሮ በደቡብ ክልል የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና ማህበራት በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸወን ሀዘን እየገለጹ ነው

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት መሪር ሀዘናቸዉን የገለጡት የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ልማት ማህበርና ፣በጋሞ ጎፋ ዞን የጨንቻ ወረዳ አመራሮች፣ ሠራተኞችና ወጣቶች፣ የክልሉ መምህራን ማህበር ጽህፈት ቤት አመራርና ሰራተኞች ፣የቡታጅራ ፍሬ ደረጃ አንድና ሁለት፣ደቡብ አድማስ ደረጃ ሶስት መለስተኛና አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር ናቸዉ ። በተጨማሪ የሲዳማ ዞን ግብርና መምሪያ አመራሮችና ሠራተኞች ፣የደቡብ ኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሞት የተሰማቸዉን ጥልቅ ሀዘን ገልጠዋል ። ተቋማቱና ማህበራቱ ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ድንገተኛ ሞት መሪር ሀዘን ያሳደረብን ቢሆንም እርሳቸው ጥለውልን ያለፏቸውን መልካም ስራዎች፣ ፖሊስዎችና ስትራቴጂዎችን በማስቀጠል ራእያቸዉን እናሳካልን ሲሉ በአንድ መንፈስ አረጋገጠዋል ። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከአባይ ወንዝ አገራችን ተጠቃሚ እንድትሆን እስከ ዛሬ የነበሩ የትኛዎቹም የኢትዮጵያ መንግስታት ያለደፈሩትን የታላቁን የሀዳሴ ግድብ ግንባታ በማስጀመር ጀግንነታቸዉን በገሀድ ያሳዩና መላዉን ኢትዮጵያዊ ያኮሩ መሪ መሆናቸዉን በመግለጫቸዉ አስታዉቀዋል ። በብልሁ መሪያቸን የተጀመሩ የልማት ስራዎችን እንዲሁም የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱን ለማሳካት ከመቼውም በበለጠ ጠንክረን እንስራለን ሲሉ በቁጭት አረጋግጠዋል ።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር