ከደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት የተሰጠ የሐዘን መግለጫ



የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ከድህነትና ኋላቀርነት ለማላቀቅ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በቅንነትና በታማኝነት አገራቸውን አገልግለው ከፍተኛ የለውጥ ተስፋ ያሳዩትን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈተ ህይወት የሰማነው በታላቅ ድንጋጤና መሪር ሐዘን ነው፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አምባገነኑን የደርግ ስርዓት ለማስወገድ በተደረገው ትግል በመታገልና በማታገል ለሀገራችን ለውጥ ታላቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ታላቅ መሪ ነበሩ፡፡ እንዲሁም ሀገራችን የህገ መንግስት ባለቤት እንድትሆንና በህገ መንግስቱና በህገ መንግስታዊ ስርዓቱ መሰረት ጠንካራ መንግስት እንዲኖራት ለማድረግ የታገሉ ግንባር ቀደም መሪያችን ነበሩ፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሀገራችን ለተመዘገበው እድገት መሰረት የሆኑ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ነደፈው ተግባራዊ እንዲደረግ ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱና በነዚህ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች አማካኝነት ለተመዘገበው እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራቸው መሪም ነበሩ፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ፣ የፌዴራል ስርዓት እውን እንዲሆን ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ፣ ዛሬ የክልላችንና የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ለተጎናፀፏቸው ራስን በራስ የማስተዳደርና በልማት አስተዋጿቸው ልክ የመጠቀም አቅጣጫ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራቸው መሪያችን በመሆናቸው የክልላችን ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የዝንተ ዓለም ባለውለታ ናቸው፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሀገራችን ብቻ ሳይሆን በአፍሪካና በአለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ችግር ፈቺ ሐሳቦችን በማመንጨትና በማፍለቅ ሀገራችንና አህጉራችን በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተደማጭነት እንዲኖራቸው ግንባር ቀደም መሪነትን የተጫወቱ በሳል መሪ ነበሩ፡፡

በመጨረሻም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና በመንግስታችን አመራር የተጀመሩ የልማትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውጥኖችን ዳር ለማድረስ የክልላችን መንግስትና ሕዝብ ከምን ጊዜውም በላቀ ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት የምንፈጽም መሆኑን እያረጋገጥን ለመላው የሀገራችን ፣ የክልላችን ህዝቦች እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፡፡
http://www.ertagov.com/amerta/erta-news-archive/49-erta-tv-hot-news-addis-ababa-ethiopia/2290-2012-08-21-18-34-16.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር