የሲዳማ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል ተከበረ
ሀዋሳ ነሃሴ 9፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) በየዓመቱ የሚከበረው የሲዳማ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል /ፍቼ ጫምባላላ/ ትናንት በሀዋሳ ከተማ ተከብሯል።
በሲዳማ ባህል አዳራሽ በተካሄደው ክብረ በዓል ላይ በተለያዩ ምሁራን የተዘጋጁ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የሲዳማ ብሔረሰብ ቋንቋው ፣ ባህሉና ማንነቱ ተክብሮለት ከሌሎች የሀገሪቱ ብሔር ብሔርሰቦች ጋር ተቀናጅቶ ለአገሪቱ ብልፅግና እየሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በስነ ስርዓቱ ላይ ተናግረዋል ፡፡
የዘመን መለወጫ /ፍቼ ጫምባላላ/ ባህላዊ የአከባበር ስነ ስርዓት በመንግስታቱ ድርጅት የሳይንስ ፣ የትምህርትና ባህል ድርጅት/ ዩኔስኮ / በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
ከዘመን መለወጫው በዓል ጋር ተያይዞ የብሔረሰቡ 18ኛው የቋንቋና ባህል ስምፖዚየም መካሄዱን ነው ኢዜአ የዘገበው፡፡
Comments
Post a Comment