ከተባበሩት የሲዳማ ፖለትካ ድርጅቶች የተሰጠ መግለጫ


በአገር ዉስጥና ውጭ ለምትገኙ ለስዳማ ተወላጆች በሙሉ 
የሲዳማ ሕዝብ የማንንም በር አንኳክቶ ደጃፉንም ረግጦ አያውቅም። ዎሮበሎችና ሌቦች ግን በተከታታይ ዘመናት ለመዳፈር
ሞክረዋል። የሲዳማ ሕዝብ ከአጼ ምንልክ ሥርወ መንግስት አንስቶ አሁን እየተንገዳገደ እስካለው የወያኔ ከፋፋይና ዋሾ መንግሥት
ድረስ ለዲሞክራሲና ለነፃነቱ የምያደርገዉን ትግል ባለማቌረጥ በየደረጃዉም ያገኟቸውን ድሎች በማጎልበት ነፃና ያልተሸራረፈ
የሥልጣን ባለቤትነት የሚረጋገጥበትን ሥርዓት ለመመሥረት ተመሳሳይ አቋም ካላቸው ኃይሎች ጋሪ ግንባር በመፍጠር ትግሉን
በማፋፋም ላይ ይገኛል።ዛሬም ትግሉ ቀጥሎ ወደ አድስ ምዕራፍ መሸጋገሪያ ደርሰናል።
አሁን ያለንበት ሁነታ በትዕብትና በጥላቻ የተዎጠረዉ ህወሃት/እሕአደግ በሕዝባችን ላይ እያደረሰ ያለው በደል ከምንግዘዉም የኬፋበት
ነው።ጥቅት ግለሰቦችን በገንዘብና በስልጣን በመደለልና መማታለል የራሳቸዉን ጥቅም ያስጠብቃሉ፡በተለያየ መልኩ ከሕዝባችን
በዘረፉት ገንዘብ መልሰዉ ሕይወቱን ለማኮላሸት ይጥራሉ፡ ብሳካላቸዉ አንድነታችንን ለማናጋትና ከፋፍለዉ ልገዙን ቀንና ሌልት
ይደክማሉ፡ ብዙዎችንም ለስደትና ለመከራ ዳርገዋል፡ለዘመናት ተከባብረን ከኖርንባቸዉ ጎሮበቶቻችን ሕዝቦች ጋር ትንኮሳን በመፍጠር
ለዕልቅት ለመዳረግ ይጥራሉ፡መሠረታዊ መብትን ለመጠየቅ የወጣዉን ሕዝባችንን በቈየዉ በግፍ ጨፍጭፈዋል።በአሁኑ ግዘ በተለይ
በህገመንግስቱ የተደነገገዉን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንድሰጠዉ ህዝባችን ለአመታት ከዳር እስከዳር እየተንቀሳቀሰ ስጠይቅ
የቆየዉን መብት ጥቅማቸውን ስለሚነካባቸዉ ከማስፈጸም ይልቅ ሕዝባችንን በእስራትና በአፈና ለማንበርከክ እየዳዳቸዉ ናችው።
አምባገነኑ መር መለስ ዜናዊ ከተሰወሩ ወራቶች ቢያልፉም ከንቀታቸው የተነሳ መርጦናል ለምሉት ሕዝብ እንኳ እዉነታዉን ትንፍሽ
አላሉም፡ ይልቁኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንቅሮ እንደተፋቸዉ ስላልተገነዘቡ የአገዛዝ ዘመናቸዉን ለማስረዘም እየዶለቱ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ ከወያኔ ባላነሰ ዲሞክራሲን የምፈሩ ተላላዎች የተዛባና የተሳሳተ ዜናዎችን  በማናፈስ በእጅጉ መስዋዕት
የከፈልንለትን የትግላችንን አቅጣጫ ለማስቀየር ይሞክራሉ።
በመሆኑም ወቅቱ ጠንካራ የጋራ ትግልና ህብረትን ከመጠየኩም በላይ ታርካዊ ግደታችንም ስለሆነ በአገር ዉስጥና ዉጭ ላላችሁ
ለሲዳማ ተወላጆች በሙሉ የምከተለውን ጥሪ እናቀርባለን፡
1.  ብዙ ወገኖቻችን መስዋዕት የከፈሉለትንና እየከፈሉ ያሉለትን የነጻነት ትግል ከዳር ለማድረስ ሁላችን በቁርጠኝ ከመቸዉም ግዜ
በበለጤ መንቀሳቀስ አለብን። ማንኛውን የሰብአዊ መብት ረገጣ መረጃዎችን እርስ በርስ መለዋወጥና አለምአቀፋዊ አካላት
እንድያዉቁት ማድረግ
2.  በውጭ የምትገኙ የሲዳማ ተዎላጀች አሁን በመካሄድ ላይ ያለውን እንቅስቃሰ በቅርብ በመከታተል በተለያዩ መገናኛ ዘደዎች
ተገብዉን ድጋፍ እንድታደርጉና በሁሉ መልኩ ከሕዝቡ ጎን እንድትቆሙ
3.   በሀገር ውስጥ የምትገኙ የሲዳማ ተዎላጆች በደል የምደርስባቸውን ወገኖች በቅርበት መከታተልና በጐናቸዉ እየቆማችሁ
የታሰሩትንና ቤተሰባቸውን መጠየቅና አስፈላግውን ትብብር እንድታደርጉ።
4.  የሕዝቡን ትግል ለማኮላሸት በባንዳነት የቆሙትን በመከታተል መረጃዎችን በማሰባሰብና በማጋለጥ በሕዝቡ እንድተፉ እንድታደርጉ
5.   የሕዝቡን የትግል አቅጣጫ ያልተከተለ ሀሰተኛ ዜናዎችንና ወረወችን የምያናፍሱ የውጭና የዉስጥ ኋይሎችን ማጋለጥና መዋጋት
6. በመጨረሻም የወያኔ ተለጣፍ የሆናችሁ በሙሉ ለማይቀረው ዲሞክራስያዊ ሽግግር ተሳታፍ ለመሆን ከወያኔ የባርነት አገዛዝ ነፃ
ለመውጣት ከሲዳማ ሕዝብ ላይ በማንሳት ከጎኑ እንድትቆሙ ኅብረቱ ጥሪ ያቀርባል።
               ድል ለሕዝባችን፡ሽንፈት ለወያኔና ለግብረአበሮቹ!!
                             USPJF
                          ነህሰ 13 2004
http://www.sidamaliberation-front.org/sidama-kai.pdf
የመግለጫውን ሙሉቃል በእንግሊዥኛ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር