የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ በሲዳምኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ድግሪ የትምህርት ፕሮግራም ሊከፍት ነው፡፡



ሃዋሳ ነሃሴ 6/2004/በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የብሄር ብሄረሰቦችን ቋንቋ ለትምህርትና ለምርምር ስራ ለማዋል እየሰራ መሆኑን የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት አስታወቁ፡፡
የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የሲዳምኛን ቋንቋን ለመጀመሪያ ጊዜ በድግሪ የትምህርት ፕሮግራም ለመጀመር መዘጋጀቱም ተመልክቷል፡፡
የሲዳምኛን ቋንቋን በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ ለማስተማር የተቀረጸው የስርዓተ ትምህርት ለመገምገምና የማዳበሪያ ሀሰብ ለማከል ትናንት በሀዋሳ ከተማ የምክከር መድረክ ተካሂዷል ።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ በምክክር መድረኩ ላይ እንደገለጹት የሀገራችን ብሄር ብሄረሰቦችን ማንነትን፣ ባህል፣ ታሪክና ወግ የሚጠናበትና የሚታወቅበት መንገድ ለማመቻቸት ራሱን የቻለ የቋንቋ ጥናት ትምህርት አስፈላጊ ነዉ ።
ዩኒቨርስቲው በደቡብ ክልል ከ54 በላይ ብሄር ብሄረሰቦች ማዕከል በሆነችው ሀዋሳ ከተማ እንደመገኘቱ አሁን በሲዳምኛ ቋንቋ በድግሪ ደረጃ የትምህርት ፕሮግራሙን ለመክፈት የተደረገዉ ዝግጅት ተጠናቆ ከያዝነው ክረምት ጀምሮ ወደ ተግባርይሸጋግራል ብለዋል ።
በሲዳምኛ ቋንቋ በድግሪ ደረጃ የሚጀምረዉ የትምህርት ፕሮግራም በማስፋፈት ወደፊት የሌሎችንም ብሄር ብሄረሰቦችን ቋንቋ በተመሳሳይ የመማሪያና የምርምር ስራ ለማዋል እቅድ መኖሩንም ዶክተር ዮሴፍ አስታውቀዋል፡፡
በተለያዩ ቋንቋዎች የመጀመሪያ ድግሪ ፕሮግራም መከፈት የብሄር ብሄረሰቦችን ባህላዊ እሴት ከማሳደግ ባለፈ ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ተናግረዋል ፡፡
የዩኒቨርስቲው የሶሻል ሳይንስና ሂዩማኒቲ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ንጉሴ መሸሻ በበኩላቸው የሲዳምኛን ቋንቋን በድግሪ ፕሮግራም በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ መሆኑን ገልጠዋል ።
በዚህ የትምህርት ደረጃ መኖሩ የብሄርሰቦች አፍ መፍቻ ቋንቋ ፣ ባህልና ማንነት ከማስተዋወቅና ከማሳደግ ባሻገር ሀገሪቱ የተቀበለቻቸው የአለም አቀፍ ስምምነቶችና ህገ መንግስታዊ መብት ጭምር ያረጋገጠ ነዉ ብለዋል፡፡
የሲዳምኛን ቋንቋ በድግሪ ደረጃ ለመጀመር ኮሌጁ ለአንድ አመት የስርዓተ ትምህርት ቀረጻን ጨምሮ የሌሎችን ግብአቶች ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ጠቁመው ስልጠናው የሚሰጠው በክረምት ለስድስት አመታትና በመደበኛ ፕሮግራም ደግሞ እንደማንኛውም የድግሪ ትምህርት ለሶስት አመታት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ትምህርቱንም ለመጀመር ከስርዓተ ትምህርት ሌላ የመምህራን ቅጥር ፣ አስፈላጊ መጻህፍትና ሌሎችንም የትምህርት ግብአቶች ዝግጅቶችን ተጠናቀው የተማሪዎች ምልመላ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመጀመሪያው የትምህርት ፕሮግራም 90 ተማሪዎችን ተቀብለው በማስተማር ወደፊት የቅበላ አቅማቸውን ለማሳደግ ዕቅድ እንዳላቸው ዶክተር ንጉሴ አስረድተዋል፡፡
የሲዳማ ዞን ምክትል አስተዳደሪና የትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ደስታ ሌንዳሞ በበኩላቸው የብሄረሰቡን ቋንቋ ለማሳደግ ዩኒቨርሰቲው በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በድግሪ ደረጃ የትምህርት ፕሮግራም መጀመሩ እንዳስደሰታቸው አመልክተው ለፕሮግራሙ ስኬት የመስተዳድሩ ድጋፍና ዕገዛ እንዳማይለያችው አረጋግጠዋል፡፡
ለሲዳምኛ ቋንቋ የድግሪ ፕሮግራም የቀረጻው የስርዓተ ትምህርት ለመገምገምና የማዳበሪያ ሀሳብ ለማከል በተዘጋጀው የግማሽ ቀን የምክክር መድረክ ላይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጡ የቋንቋ ከፍተኛ ምሁራን ልምዳቸውን በማካፈልና ጠቃሚ ሀሳቦችን በማቅረብ ፕሮግራሙ ስራ ላይ እንዲዉል ከስምምነት ተደርሷል ።

http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=1627&K=1


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር