በ5 አመቱ (2002-2007) የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና አቶ አለማየሁ አሰፋ በሲዳማ ህዝብ ላይ ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ደባ ለመፈጸም ያዘጋጁት ምስጥራዊ እቅድ ተጋለጠ




Top secret /unclassified Dossi / ከውስጥ ኣዋቂ ምንጭ(ሲዳማ ዊኪሊክ) 
የ5 አመቱ (2002-2007) ለሲዳማ የታቀደ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድና ውይይትና ውሳኔ 

ማስታወሻ፡- 
1) የዚህ ዕቅድ ውይይትና ውሳኔ ፋይል በከፍተኛ ሚስጥር የሚጠበቅ ሆኖ ለኔም የደረሰኝ በጣም ቅርብ ከሆነው ጓደኛዬና ከሁሉም በላይ ለሰው ልጅ ማንነትና መብት ከሚቆረቆር ዜጋ ነው፡፡

2) ውይይቱ የተካሄደው በሶስት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ሲሆን እነሱም፡- አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና አቶ አለማየሁ አሰፋ ናቸው፡፡ ቦታው በኃ/ማሪያም ደሳለኝ ቢሮ አ/አበባ ነው፡፡
ውይይቱ የተደረገው ከአራት ወር በፊት ሲሆን ዕቅዱ የተነደፈው በ2002ዓ.ም ሆኖ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የእቅዱ ውሳኔዎች አንዳንዶቹ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ሆኖ የዚህኛው ውይይት ውሳኔ ካለፈው በበለጠ ተግባራዊ ስለሚደረግበት ሁኔታ ነው፡፡
3) የውይይቱ ውሳኔ ሙሉ ይዘቱ ለሌሎች አምስት ም/ፕረዝዳንቶች ባሉት ብቻ የተገለፀው በአቶ ሽፈራውና በአቶ አለማየሁ አሰፋ ሲሆኑ ሌሎቹ የካብኔ አባላት ግን ሙሉውን ውሳኔ ሳይሆን ለጊዜው ተግባራዊ ለማድረግ የፈለገውን ውሳኔ ብቻ ተራ በተራ ነው፡፡
4) የትኛው ውሳኔ በምን ጊዜ በአጀንዳነት ተዘጋጅቶ ለታችኛው መዋቅር መውረድ እንዳለበ የሚወሰኑት አቶ ሽራውና አቶ አለማየሁ ናቸው፡፡
5) አንዳንድ ውሳኔዎች ለታችኛው መዋቅር በተለይም ለሲዳማ ካድሬዎች የማይወርዱ/የማይገለፁ/ እንዳሉ የሚገልፅ ቢሆንም የትኞቹ ውሳኔዎች እንደሆኑ ግን በግልፅ አያስቀምጥም፡፡
6) ወደ ውይይቱና ወደ ውሳኔው ከመግባታቸው በፊት ሦስቱም እርስ በእርስ ሂስና ግለሂስ የተደራረጉ ሲሆን በኃ/ማሪያም ላይ የቀረበው ሂስ ‘አንተ የራስህ ወገን የሆነ የአንድ ሊስትሮ ልጅ ጉዳይ እንኳን ትልቅ ሀገራዊ አጀንዳ ስታደርገው አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ግን የራሱን ወገን ’ ዶክተር ሳይል ማስትሬት ሳይል ሽማግሌ ሳይል አዛውንት፣ ወንድ ሳይል ሴት… ወዘተ ወደ ቦታው ሲመጣ በተሰጠውና ቃል በገባው ኃላፊነትና ተልዕኮ መስራት እየገነደሰ ያለ ስለሆነ ትልቅ ክብር ይገባዋል፡፡ ሌላው ሂስና ግለሂስ የተደራረጉበት ነጥብ ደግሞ አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ማንኛውንም ከፌደራልና ከክልል መግስትታት ከውጪና ከሀገር ውስጥ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የሚገኘውን ብድርና እርዳታ እንዲሁም ጥቅማ ጥቅም በቅድሚያ ለወገኑ ይሰጥ ሲል አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከላይ የተጠቀሱትን የብድር እርዳታና ሌሎች ጥቅማ ጥቅምን ብቻ ሳይሆን የገዛ ወገኑን የግልና የጋራ ሀብትና ጥቅም ተነጥቆ ለሌላው እንዲሰጥ በማድረግ የተጣለበትንና ቃል የገባበትን ኃላፊነትና ተልዕኮ በከፍተኛ አብዮታዊ ቁርጠኝነት እየተወጣ ያለ የክልሉ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው በማለት ተወድሷል፡፡
7) ከሂስና ግለሂስ ሂደት በኃላ የዚህን አጀንዳ/ዕቅድ/ ተግባራዊነት ማንኛውም እንቅፋት በመወጣት ከዳር ለማድረስ ሦስቱም ቃለመሃላ በመፈፀም የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፈዋል፡፡
8) የውይይቱ ውሳኔዎች በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ረገድ ሊከናወኑ የታቀዱ ሲሆን የውሳኔዎቹን ይዘቶች ከሞላ ጎደል ከሚስጥራዊ ሰነዱ እንዳሉ የተገለበጡ ናቸው፡፡
9) ይህ ፅሁፍ የደረሰው ማንኝውም የሲዳም ብሔር ቢያንስ ለ10 ሰዎች እንዲያስተላልፍ የአባቶች አደራ አለበት፡፡

ሀ) በፖለቲካው ረገድ መፈፀም ያለባቸው ውሳኔዎች
1. በ1997ዓ.ም የተላለፈው የሲዳማ ክልል ውሳኔ ሕገ-መንግስታዊ መሆኑን ብናምንም በአሁኑ ጊዜ የክልሉ ውሳኔ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት በኛው ካድሬዎች በህዝቡና በተለይም በወጣቱ ትውልድ ዘንድ እያቆጠቆጠና እየተቀጣጠለ ያለ እንቅስቃሴን በተመለከተ የህዝቡ አመፅና ጥያቄ ገፍቶ ጫፍ ደርሶ ከቁጥጥር ውጪ እስኪሆን ድረስ በ1997ዓ.ም የተወሰነውን የሲዳማን የክልል ውሳኔ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና ተከታዮቹ በ1998ዓ.ም ህዝቡን በመከፋፈል የተወሰነው የህብረተሰብ ክፍል በማሰር ፣ በማፈንና በማሸማቀቅ ሌላውን ደግሞ በስልጣን፣ በገንዘብና በመሬት በመደለል እንዲቀበሉት ይህንንም እንቅስቃሴ በጥቅማጥቅምና በስልጣን በመደለልና ካልሆነም በኃይል እርምጃ ማስታገስና ማስተንፈስ፡፡
2. ከፌደራል እስከ ወረደና ቀበሌ መዋቅር ውስጥ ያሉ ካድሬዎች የጥገኞቹን ስሜት የሚሸከሙ ከሆነ በተለያዩ የግምገማና ውይይት መድረኮች ስሜታቸውን እየኮረከሩ ወይም እየቀሰቀሱ ማጥራት፡፡
3. ቀድሞም ቢሆን የደህዴን/ኢህደግን አጀንዳ የሚፈታተኑትና የሚያኮላሹት በውስጥ ያሉ ልፍስፍስ ካድሬዎች ሳይሆን ከውጪ ያሉ ሙሁራንና ህዝብ በመሆኑ እነዚህን እንደተለመደው በተለያዩ ወጥመዶች እያጠመዱ ማሸማቀቅ ፣ ማስፈራራትና ማሰር፡፡
4. ከአሁን ሰዓት ጀምሮ የሀዋሳን ከተማ በስብጥር የማስተዳደሩ ዕቅድ ተግባረዊነት ለሌሎች እቅዶቻችንም ቁልፍ ሚና ያለው በመሆኑ የክልሉ መንግስትና ድርጅቱ በተለይም አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በቁርጠኝነት እንድያስፈፅሙት፡፡
5. የስብጥር ይዘት በቀጥታ ከንቲባውና ከአፈ ጉባኤው በስተቀር ሌላው ካብኔ 30% ከሲዳማ 70% ከስብጥር ሆኖ የምክትል ከንቲባነት፣የፍትህና ፀጥታና የፋይናንስና ኢኮኖሚ እንዲሁም የማዘጋጃ ዋና ስራ አስኪያጅነት ከስብጥሩ እንዲሆን፡፡
6. በፌደራል፣ በክልል፣ በሀዋሳ ከተማ፣ በሲዳማ ዞን ወረዳዎች ለሹመትና ለስልጣን የሚመለመሉ ካድሬዎች በተቻለ መጠን የሲዳማ ብሔርነት (ማንነት) ቀውስ ያለባቸው በጣም ያልተማሩ የስራና የኑሮ ልምድ የሌላቸው በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነታቸው አናሳ የሆነና…..ወዘተ እንዲሆኑ ድርጅቱና በተለይም አቶ ሽፈራው ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደርጉ፡፡
7. አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ቀድሞም እንደተወሰነውና ውጤታማ እንደሆነው አብዛኛውን ጊዜውን በሲዳማ ጉዳይ ላይ ብቻ እንዲያተኮሩ፤
8. በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚማሩትን ተማሪዎች የሲዳማነት ስሜት የሚያራምዱትን በጅምላ ማባረር
9. 12ቱን በሀዌላ ቱላ ክፍለ ከተማ ስር ያሉትን ገበሬ ማህበራትን በሀዋሳ ከተማ ክልልነት ማቀፍና ገበሬውን መጠነኛ ካሳ እየሰጡ ወደ ሌላ አከባቢ በማስፈር በነሱ ፋንታ ከሌላ አከባቢ የሚመጡትን ነዋሪዎች በማደራጀትና እገዛ በማድረግ የከተማ ቦታና ስራ፣ የመኖሪያና የንግድ ቤት በኮንዶሚኒየምና በጥቃቅን በመስራት በብድርና በአነስተኛ ዋጋ በማከፋፈል በአሁን ጊዜ በሀዋሳና አከባቢው አብላጫውን የህዝብ ቁጥር የያዘውን የሲዳማን ቁጥር ሌላው ነዋሪ እንዲበልጥ ማድረግ፡፡
10. የሀዋሳ ከተማ በስብጥር እንድተዳደር ከተደረገ በኃላ እስካሁን ከመምሪያ አንስቶ የክፍለ ከተማውና በየቀበሌው ምንም ችሎታና ትምህርት ሳይኖራቸው በሽምቅ በስልጣንና በዝምድና የተሰገሰጉትን በማስወገድ ችሎታና ትምህርት ባላቸው መተካት፡፡
11. ከዚህ በፊት በከፍተኛ ስልጣን ላይ የነበሩትንና የተወሰነ ህዝብ ተቀባይነት ያላቸውን ግለሰቦች በአንዳንድ ጥቅማ ጥቅሞች በመደለል የሁለት ወገን መልዕክተኞች እንዲሆኑ ማድረግ፡፡
12. ከላይ በተጠቀሱት መመዘኛዎች የመጡ ካድሬዎች በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን ሙሁራንና ሽማግሌዎችን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እንዲያሸማቅቁ ማበረታታት፡፡
13. እስካሁን ሲዳማ ውስጥ በመወለዳቸውና ሲዳምኛ ቋንቋ በመናገራቸው በሲዳማ ብሔርነት ተቆጥረው ለከፍተኛና ለመለስተና ሹመትና ስልጣን የበቁትን በፌደራል 2-3 በክልል 5-6 በሀዋሳ ከተማ 3-4 በሲዳማ ዞን 3-4 ያሉ ሲሆን የነሱ ሚና ብዙ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ያሉ መሆኑን በመገንዘብ እንደነሱ አይነቶቹን በጥንቃቄ በብዛት በየመዋቅሩ በብዛትና በከፍተኛ ኃላፊነት እንዲበቁ ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡
14. ሆን ተብሎ የህዝቡን ስሜት የሚቀሰቅሱ ፕሮፓጋንዳዎችንና ውሳኔችን ወደታች በማውረድ ህዝቡን በስሜት ተገፋፍቶ ወደ ሁከትና ረብሽ እንዲፈጥር በማድረግ በዚያ ሳቢያ ወታደራዊ ኃይልን በየወረዳውና በየቦታው እንዲሰፍሩ ማድረግና የስነ-ልቦና ጫና መፍጠር፡፡
15. መጠነኛ ሁከትን በጥብጠን በማጉላትና በማጋነን ማዕከላዊ መንግስትና ሌላው ህዝብ እንዲያምን ከፍተኛ የፊት ለፊትና የስውር ፕሮፓጋንዳ ስራ መስራት፡፡
16. ሁከቱንና ብጥብጡን ምክንያት በማድረግ በሰፈረው ወታደራዊ ሀይል ከህዝቡ ትጥቅ ማስፈታት፡፡
17. ባለፉት አመታት በተለያዩ የሲዳማ ድንበሮች ተግባራዊ የተደረገው የመሬት ወይም የድንበር ይገባኛል ጥያቄ የሪፈረንደም ሂደት በሌሎችም አከባቢዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥልና በፖለቲካዊ ጫና ሪፈረንደም ለሌላው እንዲያደላ ውሳኔ በመስጠት ሲዳማ በሁሉም አቅጣጫ ከሌላው ብሔር ጋር ለመሬቱ ሲል ግጭት ውስጥ እንዲገባና እንዲደክም ማድረግ፡፡

ለ) በኢኮኖሚው ረገድ ሊፈፀሙ የተወሰኑ ውሳኔዎች 

18. ሲዳማ በአሁን ጊዜ ሳይታወቅ በትምህርቱም ሆነ በኢኮኖሚው ረገድ ከሌላው የክልላችን ዞኖች ነዋሪዎች ጋር ሳይሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ እንኳን ሲወዳደር ወይም ሲነፃፀር በከፍተኛ ሁኔታ ከፍተኛ እድገት በማሳየት ላይ ያለ ህዝብ በመሆኑ ሌላውን ህዝብ ጥሎ በመሄድ በትምኪህተኝነት ስሜት ለክልሉ የበለጠ አደጋ ከመሆን አልፎ ለፌደራልም የስጋት አጀንዳ እየሆነ ያለ በመሆኑ በተቻለ መጠን እድገቱን ለማኮላሸት ዘርፈ-ብዙ ጥረት መደረግ አለበት፡፡
19. በሲዳማ ዞን ያሉ ቡና መፈልፈያዎች በጌዲኦና በሌሎች ዞኖች እንዳሉት መፈልፈያዎች በሌሎች የተያዙ ሳይሆን በሲዳማዎች ብቻ የተያዙ በመሆናቸው ለኢኮኖሚው እድገትና ለትምክህቱ መፈልፈያዎች በእጃቸው መሆናቸው ዋናው ምንጭ በመሆኑ መፈልፈያዎች በሌሎች ስብጥርነቱ እንዲያዙ የማድረግ ትልቅ ጥረት ይጠይቃል፡፡ 
20. የቡና ዋጋንና ለገበያ ማቅረቡን በተመለከተ የቡና ዋጋው በአለም ገበያ የሚዋዥ ቅበትን ወቅት በማጥናት በነዚያ ሳምንታት ገበያ ውስጥ ነጋዴዎችም ሆነ ማህበራቱ ቡናቸውን ከመጋዘን በማውጣት ለገበያ እንዲያቀርቡ በመንግስት በኩል ጫና መፍጠር፡፡
21. በዘንድሮው የአለም ቡና አቅርቦትና ዋጋ ሁኔታ አንፃር ነጋዴዎቹና ማህበራቱ በገበሬው በከፍተኛ ዋጋ እንዲገዙ ለታችኛው መዋቅር መመሪያ ማስተላለፍ፡፡
22. ከገበሬው በከፍተኛ ዋጋ የገዙ የግል ነጋዴዎችና ማህበራት በየጊዜ የአለም ኢኮኖሚ ቀውስ የተነሳ የቡናው ዋጋ ስለሚወደድ አብዛኛዎቹ መክሰራቸው ግልፅ ነው፡፡
23. ለከሰሩትም ሆነ አዲስ ለሚገነቡት የቡና ነጋዴዎች የባንክ ብድር የሚያገኙበትን ዕድል ማጥበብ፡፡
24. ባለፈው ዓመትና ከዚያ በፊት ለቡና መግዢያ ከባንክ ብድር ወስደው ሳይከፍሉ ዕዳ ያለባቸው የግል ነጋዴዎችና ማህበራት ያሲያዙትን ንብረት በሀራጅ በመሸጥ ከጨዋታ ውጪ ማድረግ፡፡
25. የባንክ እዳነት የተያዙትን መፈልፈያዎችንና ሌሎች ንብረቶችን ባንኩ ጨረታ ቢያወጣ መፈልፈያዎችን ሌሎች እንዲገዙት በብሔራዊ ባንክ አማካኝነት ለባንኮች መመሪያ እንዲወርድ ተደርጎ የመንግስት ጣልቃ ገብነት እንዲኖር፡፡
26. ለጊዜው በመንግስት መዋቅር እየተደገፉም ሆነ በራሳቸው ጥረት ደህና ደረጃ የደረሱትን ባለሀብቶች ቀስ በቀስ ከከፍታቸው እንዲወርዱና ጨርሰውም እንዲከስሩ ማድረግ፡፡ የነዚህ መውረድ ከስር እየመጡ ያሉትን ተስፋ ስሊሚያስቆርጥ ፋይዳው ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ 
27. ከገበሬው ጀምሮ ከአነስተኛ ነጋዴ እስከ ከፍተኛ ባለሀብት ድረስ ያሉትን በየከተማው ከፍተኛ የሆነ ታክስና ግብር በመጣል ማወዛገብ ማስጨነቅና ተስፋ ማስቆረጥ፡፡ 
28. ሲዳማዎች በህዝብ ብዛትና ከሌላው ዞን ህዝብ በአንፃራዊ ሁኔታ ሲታይ የተሸለ ሀብት ያላቸው በብዛት ስለሚገኙ ያላቸውን መካከለኛ ሀብትና የህዝብ ብዛት ተጠቅመው ወደ ከተማ ሀዋሳ ከተማ ቢቻ ሳይሆን ሌሎችንም የወረዳና የአከባቢ ከተማዎችን ጨምሮ መግባት መኖር መነገድና የከተማን ኑሮ ጣዕም ከቀመሱ ለሌላው በከተማዎቹ የመቀመጥም ዕድሉ በጣም ስለሚጠብ በተቻለ መጠን ሲዳማዎ ከትንሹ ከተማ አንስቶ እስከ ሀዋሳና ትላልቅ ከተማዎች የመግባት የመስራትና የመኖር ዕድላቸውን መዝጋት ካልሆነም እንዲጠብ ማድረግ፡፡
29. እንደሚታወቀው ከዘበኛው ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የመንግስት ሹመኛ ባለስልጣንና ሰራተኛ የሲዳማ ካድሬዎችንና ሰራተኞች (አሁን በስራ ላይ ያሉትንም ሆነ ከአመነታት በፊት የመንግስት ስራ ለቀው በተለያዩ የስራ መስኮች የተሰማሩትን ጭምር) ከሁለት በላይ እስከ አስር የከተማ መኖሪያና ድርጅት ያላቸው በመሆኑ በተሰራው መረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ በቅርቡ የሚወጣው የክልል ፀረ- ሙስና የሀብት ምዝገባ አዋጅ የሚፀድቅበትን ሁኔታ በማፋጠን በአዋጁ መሰረት ከአንድ ቤት በላይ ያለውን የሸጠውንም ጭምር መውረስ፡፡
30. በትምህርት በሀብት በማህበራዊ ሁኔታ ጎላ ብለው በመታየት በህዝቡ ዘንድ የአለኝታነት ስሜት የሚፈጥሩትን ግለሰቦችንና ካድሬዎችን የውሸት አሉባልታ በማናፈስ በሙስና ወንጀል፣ በፖለቲካ በማስፈራራት ከህዝብ መነጠልና ማሳሰር፤፤
31. አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከመጀመሪያው ጀምሮ የሲዳማን ትምኪት የማኮላሸት ተልኮውን ሲዳማን በወረዳ፣ በጎሳና በጎጥ በሀይማኖት በአከባቢ ወዘተ በመከፋፈል የእርስ በእርስ ቅራኔ በማስፋት የጎላ ፋይዳ ያመጣ ስለሆነ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፡፡
32. ገፍቶ የሚመጣውን የህዝብ ጥያቄና አመፅ ለማብረድ ለመሸንገያ ቃል ከሚገባው የስሙላ ግንባታና ልማት ስራ በስተቀር መደበኛ በሆነ የበጀት አመዳደብ ከሰራተኛ ደመወዝ የዘለለ በሚያስገቡት ገቢ መጠን በሚል የበጀት ምደባ እንዳይሰጥ፡፤

እንግዲህ ወገኖቼ ሌሎችም ነጥቦችና ውሳኔዎች አሉ፤፤ በነዚህ ላይ ተነጋገሩበት ለልጅ፣ ለአዋቂ፣ ለከብቱም ሆነ ለሲዳማ ምድር ሳይቀር እንዲያውቁትና እንዲመካከሩበት አድርጉ
አበቃሁ፡፡ እመለሳለሁ፡፡
የሲዳማ ህዝብ ህልዉናና ክብር ለመናድ የሚደረገዉ የደህዴን መሴሪ ተግባር በብርቱ ሲዳማ ህዝብ ትግል ይከሽፋል !!

ማስታወቂያ
ለወራንቻ ኔትዎርክ ብሎግ ኣንባብዎች ሁሉ ! 
ማንኛው ኣይነት በሲዳማ ማህባራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የምያጠነጥኑ ጽሁፎች ካሏችሁ በሚከተለው ኣድራሻ ላኩልን እኛም ለኣንባብ እናደርሳለን።
nomonanoto@gmail.com


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር