በሃዋሳ ከተማ በ60 ሚሊዮን ብር የህግ ታራሚዎችን በሙያ አሰልጥኖ የሚያወጣ ዘመናዊ የማረሚያ ተቋም በመገንባት ላይ ነዉ


 
ሃዋሳ ፎቶ ወራንቻ ኔት

ሃዋሳ 4/2004 የህግ ታራሚዎችን በተለያዩ ሙያዎች በማሰልጠን፣በእውቀት በማነጽ የክህሎት ባለቤት ለማድረግ 60 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ ዘመናዊ የማረሚያ ተቋም ግንባታ በመካሄድ ላይ መሆኑን የደቡብ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ ።
የክልሉ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽነር አቶ አዳነ ዲንጋሞ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የክልሉ መንግስት በመደበው ገንዘብ የሚካሄደው ግንባታ ታራሚዎች ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ የተለያዩ ሙያ ባለቤት በመሆን አምራችና ብቁ ዜጋ ሆነዉ እንዲወጡ ለማድረግ የሚያስችል ነው፡፡
በሃዋሳ ከተማ በመገንባት ላይ የሚገኘው ይኽው ዘመናዊ ማዕከላዊ የማረሚያ ተቋም የመመገቢያ አዳራሽ፣የህክምና ክፍል፣የመጀመሪያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ቤተ እንዲሁም የተለያዩ የሙያ ማስልጠኛ ማዕከላት፣ የመዝናኛና የስፖርት ሜዳዎችን ያካተተ መሆኑን አስታዉቀዋል ።
የማእከላዊ ማረሚያ ተቋሙ ግንባታ በሚቀጥለው የበጀት አመት አጋማሽ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡
የማዕከሉ መገንባት ታራሚዎች በቆይታቸው በሚያገኙት ዕውቀት በሀገራችን በመካሄድ ያሉ የሰላም ፣የመልካም አስተዳደርና የልማት ስራዎች ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሚያስችላቸዉ መሆኑንም አስታዉቀዋል ።
በማዕከሉ የሚገኘዉ የህክምና ተቋም በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች ሪፈር የሚጻፍላቸዉን ህሙማን ተቀብሎ እንደሚያስተናግድ ገልጠዋል ።
ከዚሁ በተጨማሪ 86 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ የወላይታ ሶዶ ፣ የዲላ፣ የሆሳዕናና የሚዛን ተፈሪ ማረሚያ ተቋማት ትምህርት ቤቶች፣ ስልጠና ማዕከልና ሌሎችንም በማካተት በአዲስ መልክ የመገንባት ለሌሎች 18 ማረሚያ ተቋማት የጥገናና የእድሳት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር