በሲዳማ ዞን ከ220 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ



ሃዋሳ ነሐሴ 9/2004 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ220 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የዞኑ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃለፊ አቶ ተሻለ ቡላዳ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከንግድ ስራ ገቢ ከማዘጋጃ ቤት፣ ቀጥታና ቀጥታ ካልሆነ ታክስና ከሌሎች የገቢ ርእሶች የተሰበሰበው ገቢ ከእቅዱ በ6 በመቶ በላይ ብልጫ አለው፡፡
ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በተደረገ ውይይትና በግብር አከፋፈል ዙሪያ በተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንዲሁም ቀደም ሲል ወደ ግብር ስርዓቱ ያልገቡ ነጋዴዎችን በመመዝገብ ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ማድረግ በመቻሉ ከዕቅድ በላይ ሊሰበሰብ መቻሉን ገልጸዋል።
ከወረዳና ከከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት የሚያስችሉ ስተራቴጅክ ዕቅድ በማዘጋጀት ተቀራርበው መስራታቸውም ለተገኘው ውጤት አስተዋጽኦ ማበረከቱን አስታውቀዋል፡፡
አዳዲስ ግብር ከፋዮች ወደ ታክስ ስርዓቱ እንዲገቡ ለማድረግ በተከናወነ ተግባር ከ300 በላይ ግብር ከፋዮች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነትና 500 የሚጠጋ ግብር ከፋዮች ደግሞ ለንግድ ትርፍ ግብር መመዝገባቸውን አቶ ተሻለ ተናግረዋል፡፡
ባለፉት 12 ወራት በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ66 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለው ገልፀዋል፡፡
አብዛኞቹ ግብር ከፋዮች ወቅታዊ ሂሳባቸውን በማሳወቅ ግዴታቸውን በወቅቱ መወጣት በመቻላቸውና የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች አገልግሎት አሰጣጣቸውን በመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጡ መሰረት በማከናወናቸው ገቢው ማደግ መቻሉን ገልጸዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር