በተጠናቀቀው በጀት አመት ከቀረቡለት 1ሺህ 4 መቶ 11 የክስ መዛግብት ለ1ሺህ 3መቶ 90 ውሣኔ መስጠቱን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ፍርድ ቤት ገለፀ፡፡


የወረዳው ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ወንድሙ ቂጤሶ እንደገለተጹት  በተጠናቀቀው በጀት አመት ጽህፈት ቤቱ ከቀረቡለት 1ሺህ 4 መቶ 11 የክስ መዛግብት ውስጥ 1 ሺ 3 መቶ 90 ዎቹ ውሣኔ መሰጠቱንና ቀሪዎቹ 21 መዛግብት ደግሞ ለቀጣዩ አመት ማስተላለፉን ተናግራል፡፡
ፍትህ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ከማድረግ አንፃር የአመቱነ አፈፃፀም 98 ነጥብ 5 ከመቶ ማድረሱን ጠቅሰው፤ ለቀጣዩ አመት መቶ በመቶ ለማድረስ ጠንክረው እየሰሩ አንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
አርሶ አደሩ ከልማት ሥራው ሣይለይ ፍተህ በአከባቢው ያገኘ ዘንድ በተቋቋሙ 4 ማዕከላት ፍትህ በመስጠት አበረታች ውጤት የተመዘገበ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ በአዲስ አመት ወደ 6 ለማሣደግ ታቅዶ እየተሠራ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
አርሶ አደሩ በህገ ወጥ ደላላዎች ይገጥመው የነበረውን የግንዛቤ እጥረት ለመቅረፍ ጧት ከችሎት በፊት በባለሙያዎች ትምህርት እየተሰጠ እንዳለ ገልፀዋል፡፡የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንደገለጸው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር