በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ላለፉት ሰባት እና ስምንት ወራት ክፍት በነበሩ የሹመት መደቦች ላይ ሰዎች መሾማቸው ተገለጸ


ከኣስተዳዳሩ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ የከተማዋን ምክትል ከንቲባ እና ንግድ እና ኢንዱስትሪ መደብን ጨምሮ በሌሎች ስድስት መደቦች ላይ ኣዳዲስ ሰዎች ተሹመዋል።

እነዚህ የሹመት መደቦች ለረዥም ወራት ሰዎች ሳይመደቡባቸው መቆየታቸው በከተማዋ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ የስራ ሂዳት ላይ ክፍተት መፈጠራቸውን ኣንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ከዚህ በፊት ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ መጠቆማቸው የሚታወስ ሲሆን፤መደባው የነበረውን ክፍተት እንደሚሞላው ታምኗል።

መደቦቹ ላይ ከዚህ በፊት እንደነበረው ሁሉ ሙሉ በሙሉ የሲዳማ ተወላጆች የተሾሙ ሲሆን፤ ሹመቱ የኣዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ከሲዳማ እጅ ልነጠቅ ነው በሚል ተነስቶ የነበረውን ህዝባዊ ንቅናቄ ሊያበርደው ይችላል የሚል ግምት ተሰጥቶታል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር