ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከሁሉም የሲዳማ ወረዳዎች ከተወጣጡ ሽማግሌዎች ጋር በክልል ጥያቄ ዙሪያ ልመክሩ ነው



ውስጥ ኣዋቂ ምንጮች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደጠቆሙት፤ ካለፈው ወር ጀምሮ በሲዳማ ዞን ውስጥ ክልልን ጨምሮ በሌሎች የመልካም ኣስተዳር ጥያቄዎች ላይ ዙሪያ በተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ በተመለከተ ከሲዳማ ሽማግሌዎች ጋር ለመምከር የክልሉ ርእስ መስተዳደር ቀጠሮ ይዘዋል።

በሚቀጥለው ማክሰኞ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው በዚሁ ምክክር ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ከሁሉም የሲዳማ ወረዳዎች ከ 40 እስከ 50 የሚሆኑ የኣገር ሽማግሌዎች የተጋበዙ ሲሆን፤ የኣገር ሽማግሌዎቹ ምንን መሰረት ባደረገ መልኩ እንደተመረጡ ኣልታወቀም።


እንደ የሲዳማ ፖለቲካ ተንታኞች ከሆነ እነዚህ ወደ ኣንድ ሺ የሚጠጉ ሽማግሌዎች የሲዳማ ህዝብ ያነሳውን የክልል ጥያቄ እንዲተው የማሳመን ስራ እንዲሰሩ በመንግስት የተመለመሉ ሳይሆኑ ኣይቀሩም።


መንግስት በቅርቡ የሲዳማ ህዝብ ያነሳውን ክልል ይገባኛል ጥያቄ  ለመቀልበስ በተለያዬ መልክ ጥረት በማድረግ ላይ ሲሆን፤ በሚቀጥለው ሳምንት የምደረገው ጉባኤ የጥረቱ ኣካል ነው።


ከኣስር ኣመት በፊት በተመሳሳይ መልኩ መንግስት ደጋፊ ሽማግሌዎችን በማሰባሰብ በወቅቱ የክልል ጥያቄ  ኣንስተው የነበሩት ሰዎች ጸረ ሰላም ኃይሎች በማስባል ማስኮነኑ ይታወሳል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር