የአስራ ሁለተኛ ክፍል መሰናዶ ተማሪዎች የፈተና ውጤት ይፋ ሆነ ፤ ለሲዳማ ተማሪዎች መልካም እድል እንመኛለን


አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 20፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስራ ሁለተኛ ክፍል መሰናዶ ተማሪዎች የፈተና ውጤት ዛሬ ረፋድ ላይ በሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ድረ ገጽ ይፋ ተደረገ።

ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን በሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ድረ ገጽ WWW. nae.gov.et መመልከት ይችላሉ።

በ2004 ዓ.ም ወደ ዪኒቨርሲቲ መግቢያ ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ቁጥር 156, 997 ነው።

የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ አራዓያ ገብረእግዚአብሔር ዛሬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ይፋ ይደረጋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር