የመልጋ ወረዳ ህዝብ ከ ፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር ሲጋጭ ዋለ


ሐምሌ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከአዋሳ ከተማ  በ26 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዋ ማልጋ ወረዳ ዛሬ በተፈጠረው ግጭት 3 የፌደራል ፖሊስ አባላት በጽኑ ሲቆስሉ ከህዝቡም በተመሳሳይ ሰዎች ቆስለዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ለእረፍት ወደ አካባቢው ከሄዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር በመሆን፣ በቅርቡ በሲዳማ ዞን የተከሰተውን ችግር እየተወያዩ በነበረት ጊዜ የፌደራል ፖሊስ አባላት  ለመበትን ጥረት በማድረጋቸው ግጭቱ መከሰቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጠዋል ”

በግጭቱ እስካሁን በፖሊስና በህዝብ ወገን ሶስት ሶስት ሰዎች ሲቆስሉ፣ ሁለት መኪኖች ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል::

ውጅግራ በሚባለው የወረዳው ከተማ 7 ሰዎች መታሰራቸውን፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት በብዛት መሰፈራቸው ታውቋል። ከታሰሩት መካከል ታምሩ በሻጋ፣ ሲናራ ሲዳሞ፣ አየለ፣ ዘለላምእንዲሁም  ደረጃ ናስሩ የሚባሉት ይገኙበታል።

በአሁኑ ጊዜ አካባቢው በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሚገኝ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ስቱዲዮ ከገባን በሁዋላ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን መረጃዎች የደረሱን ሲሆን፣ ዘጋቢዎቻችን እስካሁን ለማረጋገጥ አልቻሉም።

ቦርቻ፣ ጭኮ እና ሌሎች አካባቢዎችም ከፍተኛ ውጥረት ይታያል። ህዝቡ ከዚህ በፊት እንደነበረው ዝም ብለን አንሞትም በማለት ባገኘው መሳሪያ ሁሉ ለመከላከል መቁረጡን ነው የአካባቢው ነዋሪዎች የሚናገሩት።

በሲዳማ ዞን ከክልል እና ከመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ካለፈው ወር ጀምሮ ተደጋጋሚ ግጭት ሲከሰት  መቆየቱን መዘገባችን ይታወሳል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር