ሲዳማ ቡና አሰልጣኙን ዳኜን አሰናብቷ በቦታው ሌላ ሰው ሊቀጥር ነው የሀዋሳ ከነማው ዘላለም ሊገባ ነው ተብሎ እየተጠበቀ ነው


ማክሰኞ ሐምሌ 3 ቀን 2004 ዓ.ም
ፀጋዬ ኪዳነማሪያም የሐረር ቢራ አሰልጣኝ ቡና ገብቷል ፣ዛሬ ሲዳማ ቡና አሰልጣኙን ዳኜን አሰናብቷ በቦታው ሌላ ሰው ሊቀጥር ነው የሀዋሳ ከነማው ዘላለም ሊገባ ነው ተብሎ እየተጠበቀ ነው፣ ባንኮች ጥላሁንን አሰናብቶ ውበቱ አባተን በሀላፊነት መድቧል፣ የሲዳማ ቡናው ግብ ጠበቂ ሲሳይ ባንጫ 550ሺ ብር ተከፍሎት ደደቢት ፈርሟል፣ መሱድ መሐመድ ሌላ ክለብ 650ሺ ብር ቀርቦለታል ዛሬ ከቡና ጋር ተነጋግሯል ከጠየቀው ክለብ የቀረበለትን ገንዘብ ሰምተዋል ቡና ምን ያህል ሊከፍለው እንደሚፈልግ ማወቅ ይፈልጋል ድርድር ላይ ናቸው ፡፡ ይህን ያህል ክፈሉኝ አላለም፡፡ ከሌላ ክለብ የቀረበለትን ስለሰሙ የነሱን ዋጋ ማወቅ ይፈልጋል፡፡ የክለቡን መልስ ይጠበቃል፡፡ ቡና መሱድ፣ዳዊት ( ሞገስና እስጢፋኖስ) መዳኔ፣ሙሉዓለም ኮንትራታቸው አልቋል፡፡ የወቅቱን ገበያ አይተው ክለቡ ሊደራደር ይገባል፡፡ ጊዮርጊስ አዳነ እና ያሬድ ኮንትራታቸው አልቋል፡፡ ለዘንድሮ 1 ሚሊየን ነው የተጠየቀው፡፡ በድርድር እስከ 700ሺ ይፈረማል ነው የተባለው፡፡ ተጫዋቹ በእግር ኳሱ ለውጥ ማምጣቱ አለማምጣቱ ሳይሆን ዛሬ በፊርማ መልክ ለነገ መተዳደሪያቸው ለመስጠት የተሸለ ነው የሚሆነው፡፡ በሌላ በኩል በሴቶች በኩል የፊርማ ክፍያ እየተለመደ መጥቷል በጣም ጥሩ ጅማሬ ነው፡፡ በሴቶቹ የፊርማ የተጀመረው የዛሬ ሶስት አመት አካባቢ ነው፡፡ በ2002 ሰሚራ 3ሺ አገኘች፡፡ ባለፋው ዓመት ብርቱካን ወደ ደዲቢት ስትገባ 35ሺ በማግኘት ሪከርድ ሰበረች፡፡ አሁን ደግሞ ዳጋማዊት ወደ ባንክ በ50ሺ ብር ለመዘዋወር ስምምነት ላይ ደርሳለች፡፡ ዳጋማዊት የብሔራዊ ቡድን ተጠባባቁ በረኛ ነች፡፡\

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር