የሲዳማ ክልል ጥያቄ የሚመለሰው በኣቶ ሽፈራው በጎ ፍቃድ ሳይሆን ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት በመሆኑ ጥያቄውን በቀጠይነት ለምመለከቻቸው ከፍተኛ የፈደራል መንግስት ኣካላት እንደሚያቀርቡ የሲዳማ ሽማግሌዎች ኣስታወቁ፤ ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ በበኩላቸው የሲዳማን ክልል ጥያቄ ባለመቀበል ኣቋማቸው እንደሚገፉ ገለጹ


የሲዳማ ሽማግሌዎች

በዛሬ እለት በሲዳማ ባህል ኣዳራሽ የከተሙት የሲዳማ ሽማግሌዎች በሲዳማ የክልል ጥያቄ ዙሪያ ከደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ከኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጋር ሲመክሩ ውለዋል።

በስብሰባው ላይ ከኣንድ ወር በፊት በወጣው የማወያያ ጽሁፍ ላይ በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ በኣንዳንድ መደቦች ላይ ከሲዳማ ተወላጆች ውጪ ለማስቀመጥ እና ከተማዋን ከሌሎች ብሄሮች ጋር ለማስተዳደር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ለመወያያት የማወያያ ጽሁፍ ተዘጋጅቶ ነበር ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ኣምነዋል።

የተዘጋጀው የማወያያ ጽሁፍ በድንገት ከህዝብ እጅ መግባቱ እና የማወያያ ጽሁፉ ይዘትም ለህዝባዊ ንቅናቄ ምክንያት መሆኑን ኣስታውሰው:፤ መንግስትም ይህንን የተያዘው እቅድ መተውን እና በከተማዋ ኣስተዳደር ውስጥ ክፍት በነበሩ ቦታዎችም ላይ የሲዳማ ተወላጆች መሾሙን ተናግረዋል።

ኣክለውም  የማወያያ ጽሁፉ በማስቀረት እና ክፍት በነበሩ መደቦች ላይ የሲዳማ ተወላጆችን በመሾም መንግስት ህዝባዊ ንቅናቄውን ለመረጋጋት ጥረት ማድረጉን ጠቁመው፤ ህዝባዊ ንቅናቄ ተባብሶ ለምን ልቀጥል እንደቻሉ ሽማግሌዎቹን ጠይቀዋል።

ሽማግሌዎቹን የሲዳማ ህዝባዊ ንቅናቄ የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር ብቻ የተመለከተ ሳይሆን የክልል ጥያቄን ያነገበ መሆኑን ኣስረድተው፤ የክልል ጥያቄውን ለሚመለከተው ከፍተኛ የመንግስት ኣካል እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል።
ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ


ኣቶ ሽፈራውም ሽማግሌዎቹ ያቀረቡትን የክልል ጥያቄ እንደማይቀበሉ ገልጸው፤ ሲዳማ በደቡብ ክልል ውስጥ መሆኑ የበለጠ የልማት ተጠዋሚ ያደርገዋል የሚለውን እና ሌሎች ነጥቦችን በማንሳት የክልል ጥያቄው እንዲቀር ኣሳስበዋል።

የሲዳማ ሽማግሌዎቹም በበኩላቸው ሲዳማ ክልል መሆኑ ለህዝቡ ልያስገኝላቸው የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዎ  እድሎች በማንሳት የክልል ጥያቄው  ኣስፈላጊነት ኣስረድተዋል።

ስብሰባው ላይ ከሽማግሌዎቹ መካከል ኣስር የሚሆኑት ኣስተያየት የመስጠት እድል ኣግኝተው  የክልል ጥያቄውን በመደገፍ ተናግረዋል።

እድል ኣግኝተው ከተናጋሩ ሽማግሌዎች መካከል ከኣለታ ወረዳ መጣሁ ያሉት ፓስተር ባራሳ የተባሉ ተናጋሪ፤ መድረክ ላይ ሆነው ስብሳባውን በመምራት ላይ የነበሩትን የክልል፤ ዞን እና  የሃዋሳ ከተማ ባላስልጣናትን ስም በመጥቀስ እና ባለስልጣናቱ የሲዳማ  ተወላጆች መሆናቸውን በመግለጽ የባለስልጣናቹን ሀሳብ ሽማግሌዎቹ እንዲቀበሉ የጠየቁ ሲሆን፤ ሽማግሌዎች የተነሳውን ሀሳብ ሳይቀበሉ ቀርተዋል።

ሌላው ከዎንሾ ወረዳ መጣሁ ያሉት ሽማግሌ በበኩላቸው፤ የሲዳማ ክልል ጥያቄ የሚመለሰው በኣቶ ሽፈራው በጎ ፍቃድ ሳይሆን ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት በመሆኑ በቀጠይነት ከምመለከቻቸው ከፈደራል ከፍተኛ ኣካላት ጋር መነጋገሪን እንደኣማረጭ ኣቅረበዋል።

የስብሰባው የጠሩት  እና የመሩት ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ የሲዳማን ክልል ጥያቄ ባለመቀበል ኣቋማቸው እንደሚገፉ የገለጹ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የኣቋም ጽናት እና ኣንድነት ያሳዩት የሲዳማ ሽማግሌዎች በበኩላቸው ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው የክልል ጥያቄውን ለኣገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር እንደሚያቀርቡ ኣስታውቀዋል።

በስብሰባው ላይ ከሁሉም የሲዳማ የቀበሌዎች የተወከሉ ሽማግሌዎች እና የድርጅት ካድሬዎች መገኘቻቸው የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ዘግቧል።






Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር