የኦሮሚያ ህዝብ ለሲዳማ ህዝብ ያለውን ኣጋሪነት ኣሳየ፤ በማልጋ ወረዳ በመንግስት ሃይል እና በወረዳው ነዋሪዎች መካከል ተከስቶ በነበረው ግጭት ከሲዳማ ህዝብ ጎን በመቆም ድጋፋን ገለጸ


ከትናንትና ወዲያ በማልጋ ወረዳ ከሲዳማ የክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተነሱ ጉዳዩች ላይ ሲመክር የነበረውን የወረዳውን ህዝብ ስብሰባ ለመበተን በሞከሩ የመንግስት ልዩ ሃይል እና በስብሰባው ተሳታፊዎች መካከል ተከስቶ በነበረው ግጭት የኦሮሞ ተወላጆ ከሲዳማ ጎን በመቆም የልዩ ሃይሉን ድርጊት ተቃውመዋል።

የወራንቻ ኢንፎ ርሜሽን ኔትዎርክ ከኣካባቢው የሚወጡትን ዜናዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የኣጎራባች የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች እና ሲዳማ ለብዙ ዘመናት ኣብረው የኖሩ፤ተጋብተው  የተዋለዱ ወንድማማች ህዝቦች በመሆናቸው ኣንዱ ህዝብ ሲበደል ሌላው ቆሞ ኣያይም።

ለዚህም የኦሮሞ ህዝብ የሲዳማ ህዝብ ላነሳው የክልል ይገባኛል ጥያቄ ከመንግስት በኩል እየተሰጠው ያለው ኣሉታዊ ምላሽ ትክክለኛ ባለመሆኑ ከሲዳማ ህዝብ ጎን በመቆም ኣጋሪነቱን በመግለጽ ላይ መሆኑ ተነግሯል።

በጉጉማው ግጭት ሰው መሞቱን የተነገረ፤ ሲሆን ዘጠኝ የፈዴራል ፖሊስ እና ሶስት የወረዳው ነዋሪዎች መቁሰላቸው ተገልጿል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር