ሰበር ዜና ፦ በሲዳማ ዞን በማልጋ ወረዳ በመንግስታ ሃይሎች እና በሰላማዊ ሰዎች መካከል በተከሰው ግጭት ሰዎች መሞታቸው እና መቁሰላቸው ተነገረ


በዛሬው እለት በማልጋ ወረዳ በጉጉማ ከተማ የሲዳማ ህዝብ ለክልሉ መንግስት ለቀረበው የክልል ጥያቄዎች የመንግስት ኣካል የሰጠውን ኣሉታዎ ምላሽ በመቃዎም ተቃውሞኣቸውን በገለጹ ሰላማዊ ሰዎች እና በመንግስት ልዩ ሃይል መካከል ግጭት ተከስቷል።

ያልተረጋገጡ ከኣካባቢው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ ወደ ማታ ኣካባቢ በተከሰተው በዚህ ግጭት ሁለት ሰዎች ሞተዋል እና ሁለት ሰዎች ደግሞ በጹኑ ቆስለዋል።

ግጭቱን ተከትሎ ኣካባቢው በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ያለ ሲሆን፤ በመሆኑ በርካታ ቁጥር ያለው የመንግስት ልዩ ሃይል ወደ ኣካባቢው በመግባት ላይ መሆኑን የኣይን እማኞች ለወራንቻ ኢንፎ ርሜሽን ኔትዎርክ ገልጸዋል።

ሞቱና ቆሰሉ ስለተባሉ ሰዎች ቁጥር እና ማንነት በተመለከተ እንዲሁም ስለ መረጃው ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ወደ ኣካባቢው በስልክ ያደረግ ነው መኩራ  በኔዎርክ መጨናነቅ ምክንያት ኣልተሳከም።

ሆኖም በጉዳዩ ላይ ማረጋገጫ እና ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን ለኣንባቢዎቻችን እናሳውቃለን።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር