ከሃዋሳ ወጥቶ የነበረው የፈዴራል ሃይል ተመልሶ ገባ፤ከየወረዳዎች የተወጣጡ የኣገር ሽማግሌዎች የክልል ጥያቄን በተመለከተ ከዞኑ ኣስተዳዳሪ ጋር ያደረጉት ውይይት ያለ ውጤት ተጠናቀቀ ቀጣይ ውይይት በሚቀጥለው ሳምንት ለማደረግ ታቅዷል




ካለፈው ወር ጅምሮ የሲዳማ የክልል ጥያቄ በተመለከተ የተቀጣጠለውን  ህዝባዊ ንቅናቄን ለመቆጣጠር የሃዋሳን ከተማ ጨምሮ በኣንዳንድ የሲዳማ ወረዳዎች ሰፍሮ የነበረው የፊዴራል ሃይል ባለፉት ሳምንታት መውጣቱ የሚታወስ ሲሆን ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት በዚህ ሳምንት ውስጥ ወደ ሲዳማ  ተመልሷል።

የፈዴራል ሃይሉ ወደ ሲዳማ መመለስን በተመለከተ የተለያዩ ኣስተያየቶች እየተሰጡ ሲሆን ህዝባዊ ንቅናቄው  በተለይ በወረዳዎች ተቀጣጥሎ  በመቀጠሉ ለሃይሉ መመለስ ምክንያት ሳይሆን ኣይቀርም ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዞኑ ወረዳዎች የተወጣጡ ሽማግሌዎችን ያካተተ ኣንድ የሲዳማ ልኡካን ቡድን በትናንትናው እለት ከዞኑ ኣመራር ጋር የክልል ጥያቄን በተመለከተ የተወያይ ሲሆን ስብሳባው ያለ በቂ ውጤት ተጠናቋል።

የሲዳማ  ሽማግሌዎች ህገ መንግስቱ በምፈቅደው መሰረት የክልል ጥያቄ በሲዳማ ዞን ምክር ቤት ኣባለት እንዲቀርብ ጥያቄ  ያቀረቡ ሲሆን፤ በካላ ሚሊዮን ማትዎስ የተመራው የዞን ካቢኔ የሽማግሌዎቹን ጥያቄ ሳይቀበል ቀርቷል።

ካላ ሚሊዮን በስብሰባው ላይ የክልል ጥያቄ ከዚህ በፊት ተነስቶ የነበረ ነገር ግን በልማት ጥያቄ የተተካ በመሆኑ መልሶ ማንሳት ኣያስፈልግ የምል ኣቋም ኣንጸባርቀዋል።

በመረጧቸው እና በገዛ ልጆቻቸው ምላሽ ያልተደሰቱት ሽማግሌዎቹ የስልጣን እርከኑን ተከትለው ከላይ ካሉት ባለስልጣናት ጋር  ለመነጋገር ለሚቀጥለው ሳምንት ቀጠሮ ይዘው ተለያይተዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር