ሲዳማን ጨምሮ በዲላ ከተማ ከሶስት ዞን ለተውጣጡ የዓይን ህሙማን የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ነው


ዲላ ሃምሌ 11/2004በጌዴኦ ሲዳማና ቦረና ዞኖች በአይን ሞራ ግርዶሽና ትራኮማ ለተጎዱ ወገኖች የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ሀንሴሻ ተራድኦ ልማት ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ገለጸ።
የድርጅቱ ስራ አሰኪያጅ አቶ ታደሰ አላኮ በዲላ ከተማ ከሶስቱ ዞኖች ለተውጣጡ የዓይን ህሙማን የህክምና አገልግሎት በተሰጠበት ወቅት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት የአይን ሞራ ግርዶሽ ያለባቸውን ህሙማን በመለየት የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እየተደረገ ነው።
ባለፉት ስድስት ዓመታት በአይን ህክምናው በተለይ በዓይን ሞራ ግርዶሽና በትራኮማ የተያዙ ከሁለት ሺህ የሚበልጡ ነዋሪዎች ህክምና ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ድርጅቱ የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምናን በዝዋይና ቡታጅራ በሚገኙ የህክምና ማእከላት እንደሚሰጥ ገልጸው የትራኮማ ቀዶ ህክምናና ሌሎች ቀላል ህክምናዎችን በዲላ ሆስፒታል እየሰጠ መሆኑን አስታውቀዋል።
ማየት ተስኗቸው በቤታቸው ተቀምጠው የነበሩ 20 ልጆችን ለሶስት ተከታታይ ዓመታት የብሬል ስልጠና በመስጠት ወደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ማድረጉን አቶ ታደሰ ገልጸዋል።
በጌዴኦ ዞን የዲላ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ አቶ አለማየሁ ገመዴ ሁለት ልጆቻቸው በአይን ሞራ ግርዶሽ ማየት ተስኗቸው እንደነበር አስታውሰው ባለፈው ዓመት በተደረገላቸው ቀዶ ሕክምና ሙሉ ለሙሉ ለማየት መቻላቸውን ተናግረዋል።
በድርጅቱ አጋዠነት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከሚገኙት ተማሪዎች መካከል ተማሪ ጥላሁን ተፈራና ሁሴን መሃመድ ከዚህ ቀደም ድጋፍ የትምህርት እድል ሳያገኙ መቆየታቸውን ገልጸው አሁን ባገኙት ድጋፍ ሶስተኛ ክፍል መድረስ መቻላቸውን ተናግረዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር