በቅርቡ በሲዳማ ዞን የተከሰተውን ችግር ተከትሎ የመንግስት ሰራተኞች ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ነው


ሐምሌ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት የደቡብ ዘጋቢ እንደገለጠው በሲዳማ ዞን በዳሌ ወረዳ ይርጋለም ከተማ 3 የልማት ሰራተኞች ከስራ የተባረሩ ሲሆን ፤ ከትናንት በስቲያ ከታሰሩት መካከል ደግሞ፣ የግብርና ሰራተኞች የሆኑት አቶ ዳዊት ኡጋሞና አቶ በለጠ በልጉዳ፣ የመዘጋጃ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ዘሪሁን፣ መምህር ተስፋየ ተሻለ፣ መምህር አብዮት ዘሪሁን፣ መምህር በፍቃዱ ዱሞ፣ መምህር ለገሰ ገሰሰ፣ መምህር ዶልቃ ዱጉና እና ቀበሌ አመራሩ አቶ ካያሞ ፋቶ ይገኙበታል።

በአለታ ጭኮ ወረዳ ደግሞ የፌደራል ፖሊስ አባላት የወረዳውን ፖሊስ አዛዥ ክፉኛ በመደብደባቸው አዛዡ ሆስፒታል ተኝተዋል። አዛዡ የፖሊስ አባል መሆኑን መታወቂያውን በማውጣት ለፖሊሶች ቢያሳይም ፣ መታወቂያህን ለእናትህ አሳያት በማለት ቀጥቅጠው ደብድበውታል።  በሁሉም የሲዳማ ወረዳዎች ላይ የፌደራል ፖሊስ አባላት በብዛት ተብትነዋል። በዞኑ የሚገኙ ወረዳዎች የፌደራል ፖሊስ አባላትን ወጪ እንዲሸፍኑ በመጠየቃቸው ፣ ከክልሉ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል። የወረዳው ሀላፊዎች ለፖሊሶች ተብሎ የተያዘ በጀት በሌለበት ሁኔታ እንዴት ወጪያቸውን እንሸፍናለን የሚል ጥያቄ ቢያቀረቡም፣ የክልሉ መንግስት ለሴፍትኔት ተብሎ ከተያዘው ባጀት አውጥተው እንዲከፍሉ አዟል። አብዛኛው የሴፍትኔት ባጀት የሚያዘው ከአለም ባንክ በሚበጀት በጀት ነው።

በቀርቡ በአዋሳ እና በጪኮ ወረዳ የታሰሩት ወጣቶች ከአሸባሪው የግንቦት7 ጋር ተባብራችሁዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

______________________

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር