"ሌባ ሲነቃበት እራሱ መልሶ ሌባ ሌባ ብሎ ሰራቂና ጤነኛዉ እንዳይለይ እንደሚያደርግ፡፡ 'ድርጊታቸው/ድብቅ አጀንዳቸው ብቻ ሳይሆን ሊያደርጉ ያሰቡትም ገሀድ ስላወጣና ስለተደረሰባቸው እየተሳደቡ ያሞካሻሉ፡፡ "እንኳንስ ሲሸጡኝ ሲያስማሙኝ አውቃለው፡፡'



በፉቄ ዲሬሞ  ከሃዋሳ ሲዳማ 

ሰሞኑን መንግስት ሲዳማን ርስት አልባ ለማድረግ የሸረበውን ሴራ ለውይይት መቅረቡ መረጃ የደረሰው ሰፊው የሲዳማ ሕዝብ ተቃውሞአቸውን በተለያየ መልኩ ገልጸዋል፤ አሁንም በመግለጽ ላይ ይገኛል ፡፡ ስለሆነም ይህንን ተከትሎ ያልጠበቀው ነገር የገጠመው አቶ ሺህፈራው ሲዳማ በሬ ወልዷል በማለት ሕዝቡን ይቀሰቅሳሉ  በማለት ለማስተባበል ሞክሮ ነበር፡፡ ለመሆኑ ሲዳማ በሬ ወልዷል ሜቼ አለ? ለምን ይዋሻል? ከግብር አበሮቹ ጋር በመሆን በሬ ወልዷል ብሎ ለማሳመን በበሬ ቂጥ ላይ እንግደ ልጅ ለጥፎ እንዲሁም ደም ቀብቶ በሬ ወልዷል ስሉን ይህማ በሬ ነው በሬ ወልዶም አያውቅም ልወልድም አይችልም አልን እንጂ፡፡
     ለራሱ ተሞኝቶ የሲዳማን ሕዝብ ለማሞኘት ያደረጉትን ጥረት ከሕጻን እስከ አዋቂ ስላወገዘና  ድብቅ አጀንዳቸውን ገሀድ ስላወጡ አቶ ሺፈራዉ ሽጉጤ በደቡብ FM ሬዲዮ ሲያስተባብሉና ሲሸፋፍኑ ይባስ ብሎ  ሰፊውን የሲዳማን ሕዝብ ሌቦች/ዘራፊዎች ብሎ በሚዲያ ተሳደቡ፡፡"አባት ሲያማ; ልጅ ቢሰማ; ያያል በጠማማ፡፡'እንዲሉ ባለፈው መሬትን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው በህዝብ  ውይይት መድረኮችም ወቅት በተመሳሳይ ስድብ ዘራፊዎች ተብለን በሚዲያ መሰደባችን ይታወሳል፡፡ ዛሬ ደግሞ ያንኑ ስድባቸውን ሲያጠናክሩ ስራ አጥ ወጣቶች የሲዳማን ስምና ባህል ለማጥፋት የተሰማሩ ዘራፊዎች ሲዳማን የማይወክሉ ናቸው በማለት ለሲዳማ ማንነት፣ ባህልና ታሪክ ተቆርቋሪ ለመምሰል ሞከሩ፡፡ "የሜዳ ላይ ድብብቆሽ ይሉታል ይሄ ነዉ'
     አንድ ነገር ልብ እንበል ለዛሬው ወቅታዊ አጀንዳቸው ማለትም ሀዋሳን በስብጥር/ በጋራ እናስተዳድር ለሚለው መግቢያ እንዲሆናቸው ባለፈው "የመሬት ወረራ' የሚሉትን አስመልክቶ ሰፊውን የሲዳማ ሕዝብ ስብዕናና ሞራል በእጅጉ በሚጎዳ የስድብ መዓት ምንም ማስተካከያ ሳይደረግበት በቀጥታ በFM ሚዲያ ሲያስተላልፉ ነበር፡፡በወቅቱም የነበረውን አጠቃላይ ድባብ አስመልክቶ የFM ጋዜጠኛ ጥያቄ አንስቶላቸው ነበር፡፡ጥያቄውም እንዲህ ነው፡- "ሰሞኑን "የሀዋሳ ከተማ የፌደራል ከተማ ልትሆን/ ፌደራል ሊወስድ ነው' የሚል ወረ ይናፈሳል ይህንን እርሶ ምን ይላሉ/እንዴት ያያሉ' የሚል ሲሆን  አቶ ሺፈራው ሲመልሱ ሀዋሳን ፌደራል የሚወስድበት ምንም አግባብ የለም፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ግለሰቦች ሌላ ተልዕኮ ያሉአቸው ሲዳማን ለመቀስቀስ የሚያናፍሱት ወሬ ነው ካሉ በኃላ ሀዋሳ የክልሉና የዞኑ ዋና ከተማ ነው፡፡ የከተማው ሕዝብ ከየትኛውም ብሄር ይጠቅመኛል/ያስተዳድረኛል ያለውን ብቃት/ ቁመና ያለውን መወከል ይችላሉ በማለት መልሷል፡፡ መልሳቸውም ሰሞኑን  በሜትሮፖሊታን ከተማችንን እናስተዳድር ሚለዉ  ሴራ ቀደም ብሎ መወሰኑን ያሳያል፡፡  በአሁኑ ሰዓት ይህንን አስመሳይነታቸውን በግልጽ በመቃወም የልዕልናዉን፣ የማንነትና የባለቤትነት ድምፅ ያሰማውን ሕዝብ "አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ' እንዲሉ የብሔሩን ጥያቄ/ተቃዉሞ በስራ አጦችና በዘራፊዎች አላክከዋል፡፡
    የሲዳማ ወጣት/ተማሪዎች ከሕጻን እስከ አዋቂ የሲዳማ የህልውናው፣የክቡሩ፣ የመብቱ መገፈፍና ንቀት አንገብግቦአቸው ከእንግዲህ ይብቃን ማለታቸዉ በእውነት ዘራፊዎች ያስብላልን? እጅግ በጣም ያሳዝናል፡፡ i˜ôC møŠ~Eù°ó iUdd| „ME‰ከት ከከተሜዉ÷ †^ˆ jF´V ¬U^ i\Ô ˜M} ˆº}p †}‰ü jGmPˆU „‰üw} ¼‘ „Gj ¬^ˆðZ|‘} iM´|ኛ ብዙሃን ሲደሰኩር ተደምጧል፡፡
 አቶ ሺፈራው እራሱ  ተማሪ ማለት የለውጥ ሀይል፤ተመራማሪ፣ ሀገር ገንቢና የሀገር ተረካቢ ናቸው ማለቱ እውነት ሆኖ ሳለ ተማሪዎች ነገሮችን በስፋትና በጥልቀት ሳያዩና፡ ሳይመራመሩ በጭፍን በሌሎች ግፊት እንደሚነዱ፤ ማሰብና ማብሰልሰል እንደማይችሉ እንዲሁም የሲዳማ ህልዉና እንደማይገዳቸዉ አድርጎ መገመታቸውና መሳደባቸው"ተማሪ የለዉጥ ኃይል ነዉ!!'ብለዉ የተናገሩትን የገዛ ሀሳባቸዉን ያፋልስባቸዋል፡፡
"ሌባ ሲነቃበት እራሱ መልሶ ሌባ ሌባ ብሎ ሰራቂና ጤነኛዉ እንዳይለይ እንደሚያደርግ፡፡ 'ድርጊታቸው/ድብቅ አጀንዳቸው  ብቻ ሳይሆን ሊያደርጉ  ያሰቡትም ገሀድ ስላወጣና ስለተደረሰባቸው እየተሳደቡ ያሞካሻሉ፡፡ "እንኳንስ ሲሸጡኝ ሲያስማሙኝ አውቃለው፡፡' “Basura dichabinshanni!! በሲዳማ ሕዝብ ላይ ግልጽ ጥላቻ ያላቸውና ተፈጥሮ ያደለው ሀዋሳ መልካዓምድርና በፈጣን እድገት ላይ ከሚገኙ የሀገሪቱ ከተሞች በመጀመሪያ ረድፍ መገኘቱና ባለቤቱም ሲዳማ በመሆኑ ብቻ ሰይጣናዊ  ቅንዓት ያደረባቸው "ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ጅግራ ይሏታል' እንዲሉ የሲዳማን ብሔር ለማጥቃትና ርስት አልባ ለማድረግ ሲባል ብቻ ከተማዋ እንዳላደገችና ለዚህም ዋና መነሾ የአስተዳዳሪዎች/የሲዳማ ተሹዋሚዎች ብቃት ማነስ ነዉ በሚል / የተሸበበ ሴራ(galvanized issue) "ከተማችንን በmetropolitan እንምራ'በተሰኘ ባለ13 ገጽ የያዘ  ሰነድ ለዉይይት ማቅረባቸው/ማሰባቸው ሲመነዘር የገዛ ቤትህን/ሚስትህን መምራት ስላቃተህ  ሚስትህን አጋራኝ እንደ ማለት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ምዋርተኛ ነው ፡፡ የእነዚህ ነውረኞች የድፍረትና የንቀት ሴራቸው በሀገር ውስጥ ያሉትንና ከሀገር ውጭ ለሚገኙ ለብሔሩ ተወላጆች/በሲዳማ ብሔር ወዳጆች ዘንድ ታላቅ ቁጣ ስለቀሰቀሰ ደጋሾቹ የሚይዙትን የሚጨብጡትን በማጣት ጉዳዩን በድጋሚ ለማየት አቆይተናል/ትተናል ብለን እንዋሽ በማለት ህዘቡን ለማረጋጋት ጥረታቸውን ቀጥሏል፡፡
 ነገር ግን "ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል'ነውና ተረቱ የገመቱት ሁሉ ልክ ቢመስላቸዉም ¡\ôªN} Kšk }fm-CEô|‘} ደጋሾቹ፤ \öX ¡Nó`ki‘ iôU© ~[ i†}ªóC „‰üx} jGPˆV {iZ::
ለዚህም የሲዳማ ብሔር ተወላጆችና ወዳጆች በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚገኙ በሙሉ ሲዳማን  ታሪክና ርስት አልባ ለማድረግ የተሸረበን ሴራ ለመቀልበስና መብቱን፣ማንነቱን፣ክብሩን ለማስጠበቅ አንድ ሆነው በአንድነት ቆርጠው ተነስተዋል፡፡በዚህም የተደናገጡ "የክልሉ አስተዳዳሪ' በአሁኑ ሰዓት ሕዝቡ እኛ ወዳላሰብነው አቅጣጫ ስለሄደ አጀንዳውን በድጋሚ ለማየት አቆይተናል/ትተናል እያሉ አንዴ ላይ አንዴ ታች በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡ የትኛውን ሕጻን ለማሳመን/ለማታለል የሚደረግ ጥረት እንደሆነ በውል ባይታወቅም እነርሱ ግን ጆሮ አጥተው የሰማ ይስማ ብሎ አጀንዳውን ትተናል ይላሉ፡፡ ሌላኛዉ አስገራሚ ነገር አንዳንድ የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪዎች/ለሆዳቸዉ እንጂ ለህሊናቸዉ ማይገዙ(የፖለቲካ እቃቃ ጨዋታ የማይገባቸዉ፣ ለትዉልድ የማያስቡና ዛሬ ብቻ በልተን እንሙት ባዮች መኖራቸው ነው፡፡
 "የሰው ሞኝ አንድ እንጨት ያስራል'እንዲሉ ሲዳማ ክልል የሚሆነው ኢህአዴግ ሞቶ ሀውልት ከቆመለት በኃላ ነው፤ጥያቄያቸው የሕልም እንጀራ ነው፤"mulla agadu giira gede huguggi yite qiddaareeti mittoreno diabitanno' ያለውና ሰነዱን  ከነእንትና ከነእንትና ጋር ያረቀቀው ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ አለማየሁአሰፋና
ግብረአበሮቱ  የመላው ሲዳማ ሕዝብ ያልረሳውን ሀዘን እየቀሰቀሰ ምንም አያመጡም ያለው፤ ሲዳማን አስገድሎ/አስጨፍጭፎ እንደነ ሀይለማሪያም ደሳለኝ፣መለሰ ማሪሞ …ስልጣን ለማግኘት በቀን የሚቃዡት ይባስ ብሎ እነዚያ የሲዳማ የነፃነት ታጋዮች የተቀበሩበትን፣ አስከረኖቻቸው የወደቀበትንና ደማቸው የፈሰሰበትን ሀዋሳ ወይንም ሁለተኛ ስሙ ሲዳማ  በጋራ እንናስተዳድር ማለቱ/ ድፍረቱ የብዙዎቻችንን ቁስል አገረሽቷል፡፡ ከዚህም የተነሳ እንኳን ዛሬ ስማቸው/የሞቱበት ዓላማቸው በስፋት ተነስተው ይቅርና እንዲሁም ከማንባት ያልተቆጠቡ  እናቶች የዛሬ 10 ዓመት የልጆቻቸውን አስከሬን እንኳ ከወደቀበት ከሜዳ እንዳያነሱና እንዳያዩ በፖሊስ የተከለከሉበትን እያሰቡ እንባቸውን ይራጫሉ፡፡ ለዚህም "Hindatu lame hige Digiramanno!! ' በማለት ሰፊው የሲዳማ ሕዝብ በሀገር ውስጥ ከሀገር ውጭ የሚገኘዉ በሙሉ ሴት/ወንድ፣ህፃን አዋቂ ፣ተማሪ ሰራተኛና ነጋዴ አርሶ አደር ሳይል መብቱንና ህልውናውን ለማስከበር ከእግዚአብሔር በታች የእናቶችን እንባ ለማበስ ያለማመንታት ለመታገል በአንድነት ተነስተዋል፡፡
ከዚህም የተነሳ መንግስት እያደረሰበት ያለውን በደልና  ኢ-ሰባዓዊ ድርጊታቸውን በመቃወም የተቃውሞውን ድምፅ ከፍ አድርገው በዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና በጋዜጣ ለሕዝብ ጆር በማድረስ ሚስጥራቸውን ገሀድ በማውጣት ላይ ይገኛል፡፡  ለዚህም ግራ የተጋባው የደህዴን መንግስት ሰኔ 21ና22/04ዓ.ም በኢትዮ.ቴሌቭžን የሲዳማ ሕዝብ የክልል ጥያቄ ያነሳውና ሀዋሳ ተሸጠች ያለው የሲዳማ ሕዝብ ሳይሆን የግል ጥቅም የሚፈልጉና ጥቅማቸው የተነካባቸው ናቸው በማለት መንግስት በሚገርም ሁኔታ የዉሸት ናዳዉን በዜና በማስተላለፉ በሲዳማ ብሔር ብቻ ሳይሆን በመላው ዉስጥ አዋቂ ሕዝብ ዘንድ ሚዲያቸው ተዓማኒነትን አጥቷል፡፡
እንዲያዉም እንዲያዉ ነሽ እንኳን ዘንቦብሽ!! ይህንንም ተከትሎ በሲዳማ ዞን ባሉ 19ኙም ወረዳና 2ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ከህጻን እስከ አዋቂ መንግስት በየሚዲያዎቹ የሚሰጠውን የውሸት ማስተባቢያዎቻቸውን፣ ስድባቸውንና ለማሸማቀቅ የሚያደርጉትን ድርግት በተለያየ መልኩ አውግዟል፡፡
በተጨማሪም ሰኔ 23 2004ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በተደረገው ስብሰባ በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ቁጥራቸው ከ5000 በላይ የሚሆኑ የብሔሩ ተወላጅ ተማሪዎች ለአቶ ሺፈራዉ ሽጉጤ ካቀረቡት በርካታ ጥያቄዎች፡-
1. ጥያቄ ህጋዊና ሕገመንግስታዊ የሲዳማ የክልል ጥያቄ በአስቸኳይ እንዲመለስ የሚል ሲሆን፤
ሲመልሱ ጥያቄያችሁ ተገቢ ነው ነገር ግን ሲዳማ ክልል ማግኘት የሚችለው በ1998 ነበር በወቅቱ ብሄሩን ወክለው ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጋር የተነጋገሩ ባለሀብቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ሁለት ሁለት ኮትና 750 ብር አበል ወስደው   ለሲዳማ ክልል አያስፈልግም ለእኛ ልማት ብቻ ያስፈልገናል በማለት አጥፍተዋል፡፡ "አሁንም ክልል ለመሆን መጠየቅ ይቻላል!!' በማለት ድሮ በመድረክ እንደ አራስ ነብር የሚሆን ለዝቦ ዛሬ ቤተሰባዊ ውይይት እንወያያለን በማለት የተማሪውን ሆድ ለማባባት ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካበትም፡፡ የሚገርመው አይነቃብኝም በማለት በልበሙሉነት ለማሳመን መጣሩ ነው፡፡ በ1998ዓ.ም  የሲዳማን ሕዝብ  የክልል ጥያቄ ለመቀልበስ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ ቀንደኛ ቀንደኛ ለሆኑት/ለሆዳቸዉ ላድሩትና ጠኔ አሁኑኑ እንደሚገድላቸዉ ለሚያስቡት መሬት፣ስልጣንና ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን በማንበሻበሽ ክልል አያስፈልገንም  ልማት ብቻ በሉ ያስባለዉና ጉቦ ሰጪው/ አመቻቺዉ እራሱ አቶ ሺፈራው ዛሬ ሽማግሌዎችን ጥፋተኞች እነርሱ ናቸው በማለት ራሱን ነፃ አድርጓል፡፡ እዚህ ጋር የሲዳማ ሕዝብ መቼም የማይረሳዉ የሲዳማን ታሪክ ቀባሪዎች ሲዳማን የማሞኘታቸዉ ብዛት ምንም ጎፈሬ የሌለበት ባዶ መሬት ላልቸገራቸዉ ለዉስን(1000) የሲዳማ ብሔር ሽማግሌዎች ለክልል ጥያቄ ማባበያ እንዲሆን በሐዋሳ ከተማ 200 ካሬ(pilot of ground) በነፍስ ወከፍ መስጠታቸዉ ነዉ፡፡
2. ጥያቄ  የሲዳማ ሕዝብ የክልል ጥያቄ ያነሳውና ሀዋሳ ተሸጠች ያለው የሲዳማ ሕዝብ ሳይሆን የግል ጥቅም የሚፈልጉና ጥቅማቸው የተነካባቸው ናቸው በማለት በኢትዮጵያ ቴሌቨዥን ስለተላለፈው ዜና/ስድብ ራሱ በFM ሲዳማን ዘራፊዎች በማለት ስለተናገረው ተጠይቋል፡፡
መልስ . ሌላውን በመካድ በኢትዮጵያ ቴሌቨዥን የተላለፈውን ዜና በተመለከተ እኔ እራሴ አልተቀበልኩትም ለምን አላችሁ ብየ ደውየላቸው ነበር በማለት ዋሽተው አልፈዋል፡፡ ስለዚህ እርሶ ራስዎ  ያልተስማሙበት ከሆነ ቴሌቨዥን የተላለፈዉ ዜና ማስተባበያ/እርምት ይሰጥበት በማለት ተማሪዎቹ ተግዳሮት ፈጥረዉበት ነበር፡፡
3. በአሁኑ ሰዓት በየወረዳዎች በሰላም ሀገር የፌደራል ልዩ ሀይል በማሰማራት በሲዳማ ሕዝብ ላይ የስነ-ልቦና ጫና ለመፍጠረና ለማስገደል ያሰፈራችሃቸውን በአስቸኳይ አስወጡልን በማለት ጠይቀዋል፡፡
              ሌላው ዜና
1. ሰኔ 24/2004ዓ.ም አቶ ሺህፈራው ሽጉጤ በሀዋሳ ከተማ ሲዳማ ባሕል አደራሽ ሀዋሳን በጋራ እናስተዳድር በሚለዉ አጀንዳ ዙሪያ ለመነጋገር የዞን፣የከተማና የወረዳ አሰተዳዳሪዎችን ሰብሰቦ አወያይቷል፡፡ በዚህም ወቅት አቶ ሺህፈራው በሚለው ዙሪያ የተዘጋጀው የውይይት ሰነድ እንዴት ወደ ሕዝብ እጅ ደረሰ ለመጀመሪያ ይህንን ሰነድ የተፈራረምነው ለሰባት ሆነን ነበርን እንዴት ወጣ ካሉ በኋላ የአመራሮች ሞራል በመንካት አሸማቅቋቸዋል፤ እንዲሁም አስፈራርተቸዋል፤ የድርጅት አባል ሳትሆኑ እናንተ ተቃዋሚዎች ናችሁ ካሉ በኋላ በየወረዳዉ ወርዳችሁ ህብረተሰቡን ለሲዳማ ክልል አያስፈልግም እያላችሁ ህብረተሰቡን አሳምኑ ብለዉ ቢያሰናብቷቸዉም የአመራር ክፍሉ ያላመኑትን ለማሳመን ፈራ ተባ እያሉ ስብሰባቸዉ ተበትኗል፡፡
2. የደህዴን መንግስት ሲዳማ ለመምታት ሆነ ብለው ሲዳማዎች የወላይታ ብሔር በአሰቃቂ ሁኔታ እየገደሏቸው ነው የብዙዎቹን አንገት ቆራርጦ ሐይቅ ውስጥ እየጣሉ ናቸውና በአስቸኳይ ልዩ ሀይል ይላክልን በማለት ያስመጣው ፌደራል ፖሊስ በብሔሩ ተወላጆች ላይ ተልዕኳቻን በሚገባ  በመፈፀም በሲዳማ ብሔር ላይ ከባድ ድብደባ በማካሔድ የአካል፣በስነ-ልቦናቸው ላይ ችግር በማድረስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ለአብነትም በሲዳማ ዞን አለታ ጩኮ ወረዳ በርካታ ሰላማዊ ዜጎች በፈደራል ተደብድበው ከፍተኛ የጤና መታወክ ደረሶባቸው  ህክምና እየተከታተሉ ስሆን ሌሎቹ ደግሞ በእስራት ቤት መሆናቸው የሚታወስ ሲሆን በሲዳማ ክልል ዋና ከተማ ሀዋሳ ላይ ሰኔ 24/2004ዓ.ም  ከምሽቱ 1፡00 ገደማ  ሰላማዊ የሲዳማ ዜጎች ከሰርግ ሲመለሱ በሀዋሳ ከተማ በአቶ ወልአማኑኤል ዱባል ሀውልት አጠገብ በሲዳሚኛ እየዘመሩ ከነበሩት ሰረገኞች መካከል አንዱ በፌደራል(አጋዚ ልዩ ኮማንዶ )ፖሊስ ውስጥ የወላይታ ብሔር በሆነው  ያለምንም ምክንያት ክፉኛ ሲጎዳ ሌሎች ሰርገኞችንና በሰላም ባመሹበት ሰፈር የተኩስ እሩምታ ሰምቶ ምን ተፈጠረ ብሎ በመደናገጥና ለሰርገኞች በእነዚህ ለልዩ ሀይሎች የደረሰባቸውን መጥፎ ሀዘን ጩሄት ሰምተው ፖሊሶች የፈጠሩትን ሁከት እንደ ዜጋ ለማረጋጋት የወጣውን  የሲዳማ ብሔርና የከተማውን ሕዝብ ከምሽቱ 1፡00- 7ሰዓት ድረስ በቆየው ሁካታ በሰላማዊ ሰዎች በሲዳማ ቡና ቤት(ካፊተሪያ) ቡና በመጠጣት ላይ የነበሩትን ጨምሮ በጥቅቱ 500 ሰዎች በገዛ ቀኤያቸው፣በምድራቸውና በሰላም ሀገር ኢ-ሰብዓዊ እርምጃ/ ድብደባ ተካሂዶባቸው በአሁኑ ሰዓት ብዙዎች በራሳቸው ወጪ ህኪምና በመከታተል ላይ ናቸው፡፡
ለዚህም መንግስት ካስደበደበ በኋላ የተጎዱትንም ሆነ  የሌሎች ስሜት ለመፈተሽ ብሎ ቤት ለቤት እየዞሩ የሚጠይቁት ኮሚቴ (ሰላዮች) በማቋቋም ወደ ተጎዱት ቤት ሰዷል፡፡
ኢ-ሰብዓዊ ድብደባ ተካሂዶባቸው  
     ማሳሰቢያ ለብሔሩ ተወላጆች በሙሉ፡-
1. በአገር ዉስጥና ከዉጭ ሀገር ምትገኙ ከህጻን እስከ አዋቂ በአንድ ሀሳብ በመሆን የመጣብንን ድብቅ ጦር ለመመከት ብቸኛዉ መፍትሔ ክልል የመሆን ጥያቄአችንን መንግስት እስኪመልስ ድረስ ያለመታከት እጅና ጓንት ሆነን ያለ ምንም  ልዩነት ትግላችንን እንቀጥል!!! መንግስት ከሚያመጣዉ አስመሳይ ማባበል እንጠንቀቅ!!
2. ለሲዳማ ክልል ከተሰጠ ሌሎችም ይሰጠን ይላሉ የሚል ፍርሃት የገባው የሲዳማ ሕዝብ የነፍስ ግብር የከፈለበትንና ህገመንግስተዊ የማንነት/ የህልውናችን ራስን በራስ የማስተዳደር መብታችን/ ጥያቄአችን እንደ ጥያቄ ተቀብሎ እስኪመልስ ትግላችንን መቀጠል አማራጭ የለለው ምርጫ ስለሆነ ይህንን ለማሳካት በየትኛውም ዕድሜ ክልል፣ት/ት ደረጃ፣ስራ ላይ የሚትገኙ በሙሉ እያንዳንዱ ሰው በጣም የሚያምን/የሚቀርብ አምስት አምስት ጠንካራ ታጋዮችን በመፍጠር፣ መረጃ በመለዋወጥ ጠንካራ  መረብ በመዘርጋት ትግላችንን/ ሕልማችንን እውን ማድረግ፤
3. ሀዋሳን በጋራ እናስተዳድር የተባለው አጀንዳ ቀርቷል በማለት የሚዋሹህን እነዚያ ተላላኪዎች በሲዳማ ልጆች ደም ላይ የሚረማመዱትን ለይተህ እወቃቸው
4. ሲዳማ ማንነት/ታሪክና ስም ያለው ስለሆነ ከእንግዲህ ወዲህ በአቅጣጫ መጠራት እንደሌለበት በሚገባ ማስገንዘብ፤
5. ሲዳማን የአዳዲስ ሀሳቦች/ፍልስፍናዎች መሞከሪያ/ሙከራ ጣቢያ(centre /tools of experiment) አድርጎ መጠቀም እንደማይችሉና/ማሰብም ስህተት እንደሆነ ማስገንዘብ፤
6. ይህን ሀዋሳን በጋር እናስተዳድር የሚለው አጀንዳቸው ትተናል የሚሉት ሕዝቡን ለማረጋጋት እንጂ  በእነርሱ እምነት የማይቀር መሆኑን እንዲታውቁ ከዚህ ሀሳብ ብዙም መነታረክ እንደማያስፈልግና የሲዳማ ዋናውና ቁንጮ ዓላማ የክልል ጥያቄ ብቻ እንደሆነ ማስረገጥ፤
7. በሲዳማ ህልውና ላይ የሚመጡብህን አንተን እየመሰሉ የሚጎዱህን(ጆሮ ጠቢዎችን) ተላላኪዎችን በመለየት ከማንኛውም ዐይነት ህብረት እንዳይሳተፉ ማድረግ/የሚመለስ ከሆነ መምከር፤
8. በሲዳማ ህዝብ ጉዳይ ዙሪያ የሀገር ሽማግሌዎች ብቻ ስለሀዋሳ/ሲዳማ ይናገራሉና/ዉሳኔ ይሰጣሉና እነርሱ ይምጡ ማለት የከዚህ ቀደም እቃ እቃ ጨዋታ እንደሆነ አዉቀን ማንኛዉንም ዉሳኔ ለማሳለፍ ሕግ አወቅ/ ምሁራን የተካተቱበት መሆን እንዳለበት ሁሉም የብሔሩ ተወላጅ ጠንቅቆ እንዲያዉቅ፤
ሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ባሉ በየዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ የብሔሩ ተወላጆች ተማሪዎች ጠንካራ ህብረት በመፍጠርና ከኩታገጠምዎቻችን (በ4ቱም አቅጣጫ በድንበር ከምንገናኛቸው ጎረቤቶቻችን (ኦሮሚያ ክልል) ጋር ያለን/እያደረግን ያለነውን ወንድማማችነታችንን ማጠናከር እንዳለብን በሚገባ መገንዘብ፤
9. በሌላ ወንጀል ከታሰሩት በስተቀር በሲዳማ ሕዝብ የህልውና/በማንነት ጥያቄ የተነሳ በየትኛውም ወረዳ የታሰሩት  የብሔሩ አብራክ ክፋዮች ባስቸኳይ እንዲፈቱ ለማድረግ ሁሉም መረጃ በመለዋወጥ የጋራ አቋም መያዝ፡፡
10. መንግስት ድብቅ አጀንዳውን ለማራመድ ሲፈልግ የሌለ  ምክንያት አለመዘንጋት፤
ለምሳሌ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን የደቡብ ርዕሰ መስተዳደር ለማድረግ ተፈልጎ በፊት የነበሩትን አቶ አባተ ኪሾን በሀሰት 72000000(ሰባ ሁለት ሚሊየን )ብር መዝብåል በማለት በግፍ አስረው ከዚያም  በነፃ ለቀቀው፤ ሌሎችን እንዲሁ ማሳሰሩ ግልጽ ነው፡፡ አሁንም በሲዳማ ላይ ያላቸውን ድብቅ ጥላቻ ለመፈፀም ብዙዎችን መሬት ወረዋል፤የማስተዳደር ብቃት የላቸውም በማለት አስåቸዋል፡፡ ስለዚህ ይህንን ሴራቸውን ጠንቅቀን  እንወቅ!!!!!!!!!
ለታጋዮች          
 የዴሞክራሲ ካባ ለባሾች ቀይ ሽብር ያካሄዱባችሁ ተማራማሪዎች
እናንተ የሲዳማ አርበኞች የሲዳማ ሕዝብ የለውጥ ናፋቂዎች፤
የቁርጥ ቀን ልጆች የሲዴ ፋኖዎች፤
በእጃችሁ የያዛችሁ የሰላም ምልክት የዘንባባ ዝንጣፊዎች፤
ሰላማዊ ዘጎች የተረሸናቸሁ በኢህአደግ ባንዳዎች፡፡
ለታሪክ የሞታችሁ ሁሌም ትውልድ የሚያስታውሳችሁ፤
ሀይለማሪያም ደሳለኝ መለሰ ማሪሞ እንዲሁም…ጥይት የደገሱባችሁ፤
ያ በሜዳ ላይ/በየጥሻው ሥር እዚህም እዘያ የወደቀው ሬሳችሁ፤
ህጋዊና ህገመንግስታዊ ሆኖ ጥያቄያችው በግፍ የተረሸናችሁ፤
ሳትጨርሱ ያለቃችሁበት ያ ሕዝባዊ  አጀንዳችሁ፤
ሕጻን  አዋቂ በልቡ የያዘዉ ያረገዘዉ ጉዳያችሁ፤
ጊዜዉ ደርሷል መልስ ሊያገኝ መሻታችሁ፤ ልጠራ ስማችሁ
ሁሌም ይገለጣል ማህደራችሁ እንዲሁ ፈስሶ አይቀርም ደማችሁ፡፡
እነዚያ በእናንተ ሞት ሊከብሩ ለስልጣን ብሎ የጨፈጨፉአቸው ጨካኖች፤
በጥይት ናዳ የሬሳችሁ ማንነታት ሁሉ እስክጠፋ የዘመቱባችሁ እነዚያ ተኩላዎች፤
በፀሀይ በሜዳ በየጥሻው ስር ሬሳችሁን የጣሉአችሁ  ኢህአዴጎች፤
በሰውም በእግ/ርም ዘንድ ይጠየቃሉ እነዚያ ባንዳዎች የኢህአደግ አሸባሪዎች፡፡

ማስታወሻ፦ ከላይ በጽሁፉ ላይ የተነሱ ሀሳቦች የኣስተያየት ስጪው ኣቋም እንጂ የብሎጉ ኣይደለም።
በወቅታዊው የሲዳማ ሁኔታ ላይ ያላችሁን ኣስተያየት በሚቀጠለው ኣድራሻ e-mail: nonomanoto@gmail.com   ብላችሁ ኣድርሱን እኛም ለኣንባቢዎች እናደርሳለን።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር