ወልደ ኣማኑኤል ሃውልት ኣካባቢ ቆሞ ታክሲ እንኳን መያዝ ተከልክሏል፤በኣላሙ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ የሰፈሩት ወታደሮች የኣከባቢውን ነዋሪ እያሳቀቁ ናቸው ተባለ።


ባለፈው እሁድ ማታ ወልደ ኣማኑኤል ዱባሌ ሃውልት ኣካባቢ ሰዎች በፈዴራል ፖሊስ ከተበደቡ ወዲህ በሃውልቱ ኣካባቢ  ሌላ ግጭት ይነሳል በሚል ታክሲ እንኳን ቆሞ መጠበቅ መከልከሉ ተነግሯል።
እሁድ ማታ ላይ በተከሰተው ግጭት ወደ 150 የሚሆኑ ሰዎች በወቅቱ በፈዴራል ፖሊስ ታሰረው በዛውኑ ሌሊት የተፈቱ ቢሆንም እስከተፈቱበት ሰኣት ማለትም እስከ ከሌሊቱ ሰባት ስኣት ደረስ ክፍተኛ ድብደባ እንደተከሄደባቸው ተናግረዋል። 
ከዚህ ጋር በተያያዘ በኣላሙ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ጊዚያዊነት የሰፈረው ወታደር በኣከባቢው ከፍተኛ ጥበቃ በማድረግ ላይ ያለ ሲሆን፤ የኣከባቢውን ነዋሪ በማሳቀቅ በእለትተእለት ኑሮዎ ላይ ችግር እየፈጠረባቸው እንደሚገኝ በመግለጽ ላይ ናቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የክልሉ ኣስተዳዳሪ ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ የሲዳማን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሰብስቦ በሲዳማ የክልል ጥያቄ ዙሪያ ባናጋረበት ወቅት የሲዳማን የክልል ጥያቄ ደግፈው የተናገሩ ተማሪዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች የስልክ የማስፈራሪያ መልእክት እየደረሳቸው መሆኑን በመናገር ላይ ናቸው። 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር