ከሲዳማ ኣባት እና ከቼክ እናት የተወለደው የቼክ ሪፑብሊክ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን የተከላካይ መስመር ተጫዋች ቴውድሮስ ሃይለስላሴ ዩኩሬን እና ፖላንድ በኣንድነት ባዘጋጁትበ2012ቱ የኣውሮፓ ኣገራት የእግር ኳስ ውድድር ላይ ባሳየው ብቃት ከትላልቅ የኣውሮፓ እግር ኳስ ቡድኖች ኣይን ውስጥ መግባቱ ተነገረ




በሙሉ ስሙ ቴውድሮስ ሃይለስላሴ ጫሞላ ተብሎ የሚጠራው የቼክ ሪፑብልክ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን ተጫዋች የሲዳማና የቼክ ዴም ያለው ሲሆን፤ በኣሁኑ ጊዜ በቡንዱስ ሊጋ ለሚወዳደረው ዌርደር በሬሜን ቡድን በመጫወት ላይ ይገኛል።

የ25 ኣመቱ  ወጣት ወደ ኣገሪቱ ብሄራዊ ብድን በመቀላቀል ብሄራዊ ቡድኑ ለኣውሮፓ ዋንጫ ሽሚያ የሚያደርገውን ግስጋሴ ኣጋግሎት ለውጤት ማብቃቱ ይነጋራል።

በኣውሮፓ ሻምፕዮ 2012 ላይም ቢሆን ቴውድሮስ ኣገሩ ከግርክ ጋር ባደረገው ግጥም ላይ ከሃላ ወደፊት በረጅሙ  እየሰነጠቀ በምሰጣቸው እና ለእጥቂዎቹ ኣመቻችቶ በሚያቀብላቸው ኳሶች ኣድናቆት ማትረፉ ይታዎሳል።

ቴውድሮስ ቼክሪፑብሊክ በማጣሪያ ጫዋታዎች ስፔን ከመሳሰሉ ጠንከራ ብሄራዊ ቡድን ካላቸው  ኣገራት ጋር ባደረገችው ጫዋታዎች ላይ ያሳየው ብቃት በኣውሮፓ ትላልቅ የእግር ኳስ ቡድኖች ኣይን ውስጥ ለመግባት እንደቻለ ተነግሯል።

የቴውድሮስ ኣባት ዶክተር ገብሬ ስላሴ ጫሞላ ኢትዮጵያ በኮሚኒስት ስርኣት በምትተዳደርበት ጊዜ በተመሳሳይ መልኩ በኮሚኒስት ስርኣት ትተዳደር ወደነበረችው ወደ የቀድሞዋ ቼኮሶሎቫኪያ ከዛሬ 25 በፊት መግባታቸው እና ትዳር መስርተው ኑሮኣቸውን በዛው ማድረጋቸው የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

ከዶክተር ገብሬ ስላሴ ጫሞላ ቤተሰብ ስፖርተኛ ቤተሰብ ሲሆን፤ ኣና የምትባለው የቴውድሮስ እህት ለኣገሪቱ ለቼክሪፑብሊክ የእጅ ኳስ ቡድን እንደምትጫዎት ታውቋል።



Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር