የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለ2005 በጀት ዓመት ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ



አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/2004 (ዋኢማ) - የደቡብ ክልል ምክር ቤት በ2005 በጀት ዓመት ለሚከናወኑ የመደበኛና ካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ። የጸደቀው በጀት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ4 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ነው።

በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለብርሃን ዜና እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ በክልሉ ለሚከናወኑ የተለያዩ የመደበኛና ካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የተመደበው በጀት ብር 14 ቢሊዮን 14 ሚሊዮን 594 ሺህ 988 ብር ነው።
የበጀቱ ምንጭም ከፌዴራል መንግስት ድጎማና ከከልሉ የሚሰበሰብ ገቢ ነው፡፡
በጀቱ ለክልል ማዕከል መስሪያ ቤቶች መደበኛና ካፒታል ወጪ፣ ለዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ጥቅል በጀት፣ ለክልላዊ ፕግራሞች፣ ለሚሊኒየሙ ግብ ማስፈጸሚያና ለክልሉ መጠባበቂያ በተዘጋጀው የበጀት ማከፋፈያ ቀመር መሰረት የተደለደለ መሆኑን ገልጸዋል።
የክልሉ መንግስት ለ2005 የበጀት ዓመት ያጸደቀው በጀት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት የ4 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ሲሆን ይህም በክልሉ የሚከናወኑ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ስራዎችን አጠናክሮ ለማሰቀጠል የሚያሰችል መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም ጉባኤው በዛሬ ውሎው የክልሉ መንግስት የ2005 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ተወያይቶ ያጸደቀ ሲሆን በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና በኦዲት ቢሮ የዕቅድ ክንውን ላይ በመወያየት ዛሬ ማምሻውን ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር