ሰበር ዜና በአዋሳ በተነሳ ግጭት 1 ሰው ተገደለ 2 ሰው ቆሰለ




ኢሳት ዜና:-ባለፉት 2 ሰማንታት በአዋሳ የነበረው ውጥረት እየተባባሰ በመምጣት ላይ ሲሆን፣ ትናንት ማታ በፌደራል ፖሊስና በህዝቡ መካከል በተነሳ ግጭት 1 ሰው ሲገደል ሁለት ደግሞ ቆስለዋል።

ግጭቱ የተነሳው በአዋሳ ከተማ ወልደአማኑኤል ዱባለ አደባባይ አካባቢ የተካሄደውን የሰርግ ስነስርአት ተከትሎ ነው። የሲዳማ ወጣቶች በሲዳምኛ እየጨፈሩ ሙሽሮችን ለመቀበል ሲሄዱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ተኩስ ከፍተውባቸዋል። በፖሊሶች ድርጊት የተበሳጩት የከተማዋ ነዋሪዎችም በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ድንጋዮችን በመወርውር ተቃውመዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላትም ተቃውሞን ለመበትን በርካታ ጥይቶችን ሲተኩሱ አድረዋል።

በዛሬው እለትም በአንዳንድ አካባቢዎች የተኩስ ድምጽ ይሰማ ነበር። ከባድ መሳሪያዎችን የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን አጨናንቀው መዋላቻውን፣ ውጥረቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱንና በማንኛው ጊዜ የከፋ ግጭት ሊነሳ እንደሚችል በስፍራው የሚገኘው ዘጋቢያችን ገልጧል።

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣  የግብርና ሰራተኞች፣ መምህራን፣ የክልሉ ፖሊስ ተወካዮች፣ የምክር ቤት አባላትና  እና ሌሎችም ከ 300 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ባለፈው ቅዳሜ በአዋሳ ከተማ በህቡእ ተሰባስበው የሲዳማ ወጣቶች ንቅናቄ የሚል ድርጅት መመስረታቸውን መግለጣችን ይታወሳል።

______________________

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር