ሲኣን የሲዳማ ህዝብ ህገ መንግስታዊ ክልል የመሆን ጥያቄ በኣስቸኳይ እንድመለስ ጠየቀ፤ በሲዳማ ህዝብ ስም እየነገዱ የሲዳማን ማንነት ለመሸጥ የምሯሯጡ ጥቂት ኣድርባዮች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ኣስጠነቀቀ::

New

ሲኣን የሲዳማ ህዝብ ህገ መንግስታዊ ክልል የመሆን ጥያቄ በኣስቸኳይ እንድመለስ ጠየቀ፤ በሲዳማ ህዝብ ስም እየነገዱ የሲዳማን ማንነት ለመሸጥ የምሯሯጡ ጥቂት ኣድርባዮች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ኣስጠነቀቀ::
የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ሲኣን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የሲዳማ ህዝብ በህገ መንግስቱ የተሰጡትን የዲሞክራሲያዊ መብቶች ህጉና ደንቡን መሰረት በማድረግ በሰላማዊ መንገድ ስጠይቅ መቆየቱን ኣስታውሶ ከተጠየቁት ጥያቄዎች ኣንዳቸውም ተጨባጭ ምላሽ እንዳላገኙ ኣመልክቷል::
የሲዳማ ህዝብ የጠየቀው ክልል የመሆን ጥያቄ በህገ መንግስት የተደነገጉውን ክልል የመሆን ቅድመ ሁኔታ በተገቢው መልኩ ያሟላ ቢሆንም ገዥው ፓርቲ ለራሱ ኣገዛዝ እንዲመቸው ሲል ጥያቄውን በልማት ሽፋን ሳይመልስ መቆየቱን ጠቅሶ፡ ኣሁንም ቢሆን በድጋሚ የተነሳው የክልል ጥያቄው በኣግባቡ እንዲመለስ ጠይቀዋል::
ኣያይዞም በሲዳማ ህዝብ ስም እየነገዱ የህዝቡን ማንነት ለማሸጥ የምሯሯጡ ኣድርባዮች ከድርጊቻቸው እንዲቆጠቡ ኣስጠንቅቋል::

የጋዜጣዊ መግለጫውን ሙሉ ቃል በሚቀጥላው ሊንክ ይመልከቱ:
የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ሲኣን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር