የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ አሁን የተነሣ ሳይሆን ለዓመታት ሲታገልለት የቆየ መሆኑን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ አስታወቀ፡፡




ኢሕአዴግ በ1984 ዓ.ም አምስት የነበሩትን ክልሎች ወደ አንድ በማምጣት አሁን ደቡብ የሚባለውን ክልል የፈጠረበት ሁኔታም ድንገተኛና የሚመለከታቸው ያልመከሩበት ነው ሲሉ የክልሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተችተዋል፡፡
የሲዳማ አርነት ንቅናቄ - ሲአን ለሰጠው መግለጫ መነሻ የሆነው የሃዋሣ ከተማን ዕጣ ፈንታ አስመልክቶ በክልሉ ገዥ ፓርቲ ለውይይት ቀረበ የተባለው ሠነድ ነው፡፡
ሜትሮፖሊታን ከተማችንን እንዴት እንምራው በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ሠነድ ከግንቦት 27 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ለውይይት መቅረቡን ፓርቲው አስታውቋል፡፡
ሠነዱ ለውይይት የቀረበውም ለሲዳማና ለሃዋሣ ከተማ አስተዳደር የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ለሲዳማ ተወላጅ የደኢሕዴን አባላት መሆኑን ጠቅሷል፡፡
ሠነዱ ሃዋሣ በተለያዩ ብሔረሰቦች ስብጥር እንድትተዳደር የሚጠይቅ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡
ይህንን ሠነድ አጥብቆ እንደሚቃወመው የገለፀው ሲአን የዞኑ ተወላጆችም ይቃወሙታል ባይ ነው፡፡
ፓርቲው በዚሁ መግለጫ የሲዳማ ሕዝብ “ክልል የመሆን ጥያቄ”ም ሊመለስ ይገባል ሲልም አሣስቧል፡፡
የሃዋሣው ሠነድ ጉዳይ ወቅታዊ ይሁን እንጂ የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ በተደጋጋሚ የተነሣና ሲታገልለት የቆየ መሆኑንም ሲአን አስታውቋል፡፡
ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡


ሜትሮፖሊታን ሃዋሣ እና “ክልል” ሲዳማ እያነጋገሩ ነው

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር