የሲዳማ ህዝብ ንቅናቄ በተመለከተ ኣስታያየቶች እየጎረፉ ነው

ከኣስታያዬቶቹ መካከል፥
የዳንግላው ዋርካ ተብሎ በሚታወቀው ትልቁ የኢትዮጵያውን ዌይብ ሳይት ላይ እንደጻፈው:
የሲዳማ ሕዝብ በሀዋሳ ከተማ ባለቤትነት ጥያቄ በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ባለፉት 3 ቀናት ውስጥ በአዋሳ ከተማ በፌደራል / ወያኔ መልዕክተኞችና በሲዳማ ክልል የፓርላማ ተወካዮች መካከል በተደረገው ፍጥጫ የሲዳማ ተወካዮች ጉባኤውን ረግጠው ሲወጡ በርካታ የሲዳማ ተወላጅ ባለሀብቶች : ባለስልጣኖችና ተማሪዎች ከየቤታቸው በሌሊት እየታፈኑ እየታሰሩ ሲሆን አንድ ግለሰብ በአጋዚ ተደብድቦ ሕይወቱን አጥቷል :;

ከተማዋ በአጋዚ ሠራዊት ታንክና ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ሄሊኮፕተሮች በብዛት እያንዣበቡባት ነው :: አዋሳ ባሁኑ ጊዜ በፍርሐትና በጭንቀት ተውጣለች ::

ሲዳሞች ሲዳማ ሕዝብ በአዋሳ ከተማ የዞን ዋና መሥሪያ ቤቶች አዋሳ ውስጥ እንዳይኖሩ በከተማዋ ውስጥ ሲዳሚኛ እንዳይነገሩ ባህላችን ተገፍትሮ ከገዛ ወገኑ እንዲርቅ ተገዷል ይላሉ ::

ኃ /ማሪያም ደሳለኝ ከ 6 ዐመት በፊት የሲዳማ ተወላጅ የሆነውን የቀድሞ የደቡብ ፕሬዚዳንት አባተ ኪሾን በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ በገዛ ፊርማው ከሥልጣን አባሮ በወንበሩ ላይ ጉብ ብሎ ፕሬዚዳንት እንደሆነ ይታወሳል :: በጊዜው በተነሳውም ረብሻ የ 121 ሰው ሕይወት ከጠፋ በኋላ ወንጀለኛው ኃይለማሪያም ፕሮሞት ተደርጎ ላሁኑ ቦታ እንደበቃ ይታወቃል ::

አሁን ደግሞ የክልሉ መደበኛ ስብስባ ሲደረግ የሲዳማ ተወካዮች ሁሉም ባንድ ቃል መብታችን ይከበርልን ብለው ሲጠይቁ አምባገነኑ ኃይለማሪያም ይህን ጥያቄ ደጋግማቹ የምታነሱ ከሆነ አዋሳ ይገባናል ካላችሁ የደቡብ ዋና ከተማ ወደ ራሴ ትውልድ ቦታ ወላይታ ሶዶ ይሆናል ብሎ አረፈው ::        
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
   



yoni_love
የተባለ ግለሰብ የሰጠው ምላሽ:



Joined: 02 Jan 2005
Posts: 123
Location: Baltimore
Posted: Thu Jun 21, 2012 8:39 am    Post subject: Re: ኃ /ም ደሰሳለኝ የደቡብ ዋና ከተማ ወላይታ ይሆናል አለ
የዳንግላው እንደጻፈ(ች)ው:
አዋሳ ይገባናል ካላችሁ የደቡብ ዋና ከተማ ወደ ራሴ ትውልድ ቦታ ወላይታ ሶዶ ይሆናል ብሎ አረፈው ::        


   ይታያቹ አለቃው መለስ ታሞ ጎስት መስሏል :: ቦነስ ቀን ከአምላክ ብለስ ካልተደረገለት ምናልባት የሚቀረው ጊዜ 1 ዐመት ነው አሉ :: ኢማጂን ይህ አጎዛ እሱን ተክቶ ጠ /ሚኒስትር ሲሆን ይታያችሁ     በቅርቡ አገራችን ሌላኛውን ኤዲያምኒን ዳዳን ታሳየናለች ማለት ነው :: ያውጣን
_________________
Small world
http://www.cyberethiopia.com/warka5/viewtopic.php?t=48934

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር