በመላው ኣለም ላይ የሚገኙ የሲዳማ ዳይስፖራ በሲዳማ ዞን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ንቅናቄ በንቃት በመከታተል እና በመደገፍ ላይ መሆናቸውን ገለጹ።


የዳይስፖራው ተወካዮች ለሲዳማ ወራንቻ የኢንፎርሜሽን ማእከል በላኩት መልእክት እንዳስታወቁት፤ የሲዳማ ህዝብ ያነሳቸውን የመልካም ኣስተዳደር እና የክልል ጥያቄዎችን ይደግፋሉ ለተግባራዊነቱም ከዞኑ ህዝብ ጎን ይቆማሉ።

በሰሜን ኣሜሪካ፡ በታላቋ ብርታኒያ፡ በኖርዌይ፡ በኔዘርላንድ፡ በመካከላኛው ኣውሮፓ ኣገራት፡ በህንድ፡ በሳውድ ኣረቢያ እና ደቡብ ኣፍሪካ ነዋሪ የሆኑት የዞኑ ዳይስፖራ ኣባላት ህዝባዊ ንቅናቄውን በቅርበት በመከታተል ላይ መሆናቸውን ኣስታውቀዋል።

ህዝባዊ ንቅናቄው ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በንቅናቄው ላይ የኣለም ህዝብ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖረው በተለያዩ የዜና ኣውታሮች የሚቀርቡ ዘገባዎች ከህዝባዊው ንቅናቄ ኣላማዎች ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ የማደረግ ስራ በመስራት ላይ መሆናቸውን ኣስረድታዋል።

ኣያይዘውም ለህዝባዊ ንቅናቄ መሳካት ኣስፈላጊውን ደጋፍ ለማደረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር