በሲዳማ ዞን እየተነሳ ባለው ተቃውሞ የመንግስት እጅ አለበት ተባለ



ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአዋሳ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት ለዘመናት ተቻችለው የኖሩ ህዝቦች እንዲጋጩ ለማድረግ የመንግስት ባለስልጣናት ሆን ብለው እየሰሩ ነው። ህዝቡ በኑሮ ውድነቱ፣ በመብት አፈናው እና በተለያዩ አስተዳደራዊ ችግሮች እየተማረረ፣ ከዛሬ ነገ ለውጥ ይመጣል እያለ በሚናፍቅበት በዚህ አስቸጋሪና አስፈሪ ወቅት፣ መንግስት የዋሳ ከተማን አስተዳደር እንደገና የህዝብ አጀንዳ አድርጎ በማቅረብ ግጭት እንዲነሳ መጣሩ ነዋሪዎችን አስቆጥቷል።

የዞኑ ባለስልጣናት የሚያስወሩት ዘርን ከዘር የሚያጋጭ ወሬ የከተማው ህዝብ የፍርሀትን ካባ እንዲደርብ እንዳደረገው ነዋሪዎች ይገልጣሉ። በዛሬው እለት ዳቶና  መምቦ በተባሉ አካባቢዎች ተማሪዎች ያሰሙትን ተቃውሞ ተከትሎ ዘርፊያ መካሂዱን፣ መኪኖች ታግተው መዋላቸውን ዘጋቢዎቻችን ገልጠዋል። በከተማዋ አሉ ሱቆች ዝርፊያ በመፍራት ተዘግተው መዋላቸውን ለማወቅ ተችሎአል። በዳቶና መምቦ አካባቢዎች የፌደራል ልዩ አድማ በታኝ ፖሊሶች በአስለቃሽ ጭስ ተቃውሞውን ለመቆጣጠር መቻላቸውን ውጥረቱ ግን አሁንም መኖሩን ዘጋቢዎች ገልጠዋል።

ግጭቱ  ከአዋሳ ከተማ እጣ ፋንታ አልፎ የዘር ጉዳይ እየሆነ መምጣቱ፣ የከተማውን ህዝብ ለሁለት መክፈሉም እየተነገረ ነው። የሲዳማ አገር ሽማግሌዎች ለዘመናት ተፈቃቅሮ የኖረውን ህዝብ የሚያበጣብጠው መንግስት በመሆኑ ተቃውሞው ሁሉ መንግስት ላይ እንዲሆን ወጣቶችን የማሳመን ስራ እየሰሩ ነው። የሲዳማ ተወላጅ ያለሆኑ የአዋሳ ነዋሪዎች ጥያቄው ከዘር አልፎ አገርአቀፍ አጀንዳ ይዞ ከመጣ ሊቀላቀሉዋቸው ዝግጁ መሆናቸውን እየገለጡ ነው።

አንድ ስሙን መግለጥ ያልፈለገ ወጣት ችግሩ እንዲህ በቀላሉ ይፈታል ብሎ እንደማያምን ገልጦ ፣ ተቃውሞውን ወደ ችግር ፈጣሪው መንግስት ማዞር ብቸኛ መፍትሄ ነው ብሎአል።

http://www.ethsat.com/

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር