አቡነ አብርሃም ወደ ሀዋሳ ለመዛወር ያላቸውን ጉጉት ይፋ ማውጣት መጀመራቸው ተሰማ


በብዙዎች ዘንድ አቡነ ገብርኤል ከሀዋሳ እንደሚነሱ እየታመነበት የመጣ ይመስላል፡፡ በአንድ ወቅት ማኅበረ ቅዱሳኖች የእኛ ሊቀጳጳስ አቡነ ገብርኤል ናቸው ብለው እንዳልጮኹ ሁሉ ዛሬ ደግሞ በግፍ ከተሰደዱት የሀዋሳ ምዕመናን ይልቅ በእነርሱ ብሶ ዓይንዎትን ለአፈር ብለው ከአካባቢያቸው እስኪለቁላቸው ተጣድፈዋል፡፡

በዚህም መሠረት እጅግ ብርቱ በሆነ ሚስጥራዊ ሁኔታ የማቅ አባላትን ፊርማ በሀዋሳ ምዕመናን ስም አስመስለው ያሰባሰቡ ሲሆን፣ በምትካቸው ገና ከወጣትነት አፍላ ያልተላቀቁትን አቡነ አብርሃምን ከሐረር ወደ ሀዋሳ ለማዛወር ማቀዳቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ዓለማውያኑ "አልመጣም ቀረሁኝ፣ ከአንቺ የተሻለ ከዚህ አገኘሁኝ" ብለው እንደገጠሙት፣ ማቆች ሀዋሳን ለመቆጣጠር ለአቡነ ገብርኤል "ከእርስዎ የተሻለ፣ ከሐረር አገኘን" ብለው እንደገጠሙላቸው በየዓይነ ኅሊናችን መሳል እንችላለን፡፡

በዚህ ሁኔታ የተበረታቱት አቡነ አብርሃምም የየሊቃነጳጳሳቱን በር እያንኳኩ መሆኑን ውስጥ ዐዋቂዎች ገልጸዋል፡፡ ባለፉት ሥርዓቶች በየመኳንንቱ እና በየነገሥታቱ ፊት ደጅ ሲጠና እንደሚደረገውም ለእጅ መንሻ የሆነች ነገር ሸጎጥ እያደረጉ መሆኑንም እነዚሁ ውስጥ ዐዋቂዎች ጠቆም አድርገዋል፡፡ ደጅ ከተጠኑት ሊቃነጳጳሳትም መካከል ብፁዕ አቡነ  ሉቃስ የመተማ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የመጀመሪያው ሲሆኑ እኝህ አባት ሀዋሳ ላይ የሚገኘውን መኖሪያ ቤታቸውን ለማኅበረ ቅዱሳን የንዑስ ማዕከሉ ጽ/ቤት ሆኖ እንዲያገለግል መስጠታቸው ታውቋል፡፡

አቡነ አብርሃም "ምነው ሐረርን ጠሉ? ሀዋሳን ወደዱ"? ተብለው ሲጠየቁ የሐረር ችግር አላኖር ብሎኛል፡፡ ሰልችቶኛል እያሉ መልስ እየሰጡ ናቸው ተብሏል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን ትተው ቤተክርስቲያንን ማገልገል እስካልጀመሩ ድረስ የትም ቢሆን መቸገራቸው አይቀርም፡፡ እንዲያውም የሀዋሳው ባይብስባቸው ነው?
http://dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com/2012/05/blog-post_08.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር