የሲዳማን ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብት መጣስ ማለት የኢትዮጵያን ህገ መንግስት መናድ ስለሆነ ሁሉም ብሄርና ብሄረስብ ከሲዳማ ህዝብ ጎን ሊቆም እንደምገባ ተገለጸ:: በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ 30 ከመቶ የሚሆነውን የኣስተዳደር ቦታ በሌሎች ብሄር እንዲያዝ በሚል የተቀመጠውን የኢህኣዴግ ኣቅጣጫ የሲዳማን ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብቱን የጣሰ ነው በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል::

New

የሲዳማን ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብት መጣስ ማለት የኢትዮጵያን ህገ መንግስት መናድ ስለሆነ ሁሉም ብሄርና ብሄረስብ ከሲዳማ ህዝብ ጎን ሊቆም እንደምገባ ተገለጸ::

በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ 30 ከመቶ የሚሆነውን የኣስተዳደር ቦታ በሌሎች ብሄር እንዲያዝ በምል የተቀመጠውን የኢህኣዴግ ኣቅጣጫ የሲዳማን ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብቱን የጣሰ ነው በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል::

እስከ ኣሁን በይፋ ያልተነገረው ነገር ግን ለወራት ውስጥ ለውስጥ በህዝቡ ዘንድ ስወራ የቆየው በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ ከሲዳማ ብሄር ውጪ ሌሎች ብሄሮችን የመቀላቀል ጉዳይ በተለይ የሲዳማ ተወላጆች ክፉኛ ያስቆጣ ሲሆን የኢህኣዴግ መንግስት በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ያለውን ደጋፊ ሊያሳጣው ይችላል ተብሏል::  

ጉዳዩን በትኩረት ስጥተው በመከታተል ላይ የሚገኙ ግለሰቦች እንደምሉት ከሆነ፥ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት የኣገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብት ካጎናጸፈ ከ 20 ኣመታት በኋላ የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር የሲዳማ ህዝብ ከሌላው ብሄር ጋር እንድጋራ ለማድረግ የምደረገው እንቅስቃሴ የኣገሩቱን ህገ መንግስት እንደመናድ ይቆጠራል::

የኢህኣዴግ ኣመራር በራሱ ኣስተዳደር ውስጥ ያለውን የመልካም ኣስተዳደር ችግር ለመቅረፍ ኣጥጋቢ የሆነ እርምጃ ካለመውሰዱ በላይ በመልካም ኣስተዳደር እጦት በመሰቃየት ላይ የምገኘው የሲዳማ ህዝብ እራሱ በራሱ የማስተዳደር መብት ለማፈን እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ '' እንኳን ዘንባብሽ ….'' ኣይነት እንደሆነባቸው ኣንዳንድ የብሄሩ ተዋላጆች ተናግረዋል::

በከፍተኛ የኢህኣዴግ ኣመራሮች ሊወሰድ ነው እየተባለ የሚገኘውን ይህን ውሳኔ በሲዳማ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በራሱ በ ኢህኣዴግ ካድሬዎችም ጭምር ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን: ውሳኔውን በተመለከተ የሲዳማን ህዝብ ለማሳመን ሃላፊነት የተሰጣቸው የኢህኣዴግ ካድሬዎች  ራሳቸው ጭምር  በጉዳዩ ዙሪያ ከህዝቡ ጋር ለመነጋገር መፍራቻቸው እየተነገረ ነው::

በኣሁኑ ጊዜ ህዝባዊ ተቃውሞ ከዳር እስከ ዳር የተቀጣጠለ ሲሆን በተለይ በወረዳዎች ያለው ህዝብ በጉዳዩ ዙሪያ የሚያና ግራቸውን መንግስታዊ ኣካል በመጠባበቅ ላይ ናቸው::

የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ጉዳይ በበርካታ የሲዳማ ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት የምሰጠው ጉዳይ ሲሆን የዛሬ ኣስር ኣመት በተመሳሳይ መልኩ የኢህኣዴግ ኣመራሮች የሲዳማን ህዝብ ሳያማክሩ በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ ከሲዳማ ብሄር ውጪ ሌሎች ብሄሮችን ለመቀላቀል ያሳለፉት ውሳኔ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመውና ተቃውሞኣቸውን በሰላማዊ ሰልፍ የገለጹ የሲዳማ ተወላጆች መካከል ከ50  የሚበልጡት በመንግስት የጸጥታ ኋይሎች መገደላቸውና በሺዎች የምቆጠሩት ደግሞ መታሰራቸው ይታወሳል::

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር