የኢጋድ አባል ሀገራት የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና አፋጣኝ ምላሽ ሜካኒዝምን (ሲዋርን CEWARN) አቋቋመው እንቅስቃሴ ከጀመሩ ወዲህ በቀጣናው ድንበር ዘለል ግጭቶች እየቀነሱ መጥተዋል ተባለ፡፡


የኢጋድ አባል ሀገራት የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና አፋጣኝ ምላሽ ሜካኒዝምን (ሲዋርን CEWARN) አቋቋመው እንቅስቃሴ ከጀመሩ ወዲህ በቀጣናው ድንበር ዘለል ግጭቶች እየቀነሱ መጥተዋል ተባለ፡፡የሜካኒዝሙ ጥረት በሀገራቱ መሀከል መተማመንና በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ አብሮ የመስራት ልምድ እንዲያዳብሩ አስተዋፅኦ ማበርከቱንም ገልጿል፡፡
ሜካኒዝሙ ለሚቀጥሉት 8 ዓመታት የሚመራበት አዲስ ስትራቴጂ በመንደፍ ላይ መሆኑን አመልክቷል፡፡የኢጋድ አባል ሀገራት በአርብቶ አደሩ አካባቢ የሚከሰቱት ድንበር ዘለል ግጭቶችን በማስወገድ አካባቢው አስተማማኝ ስላም ያለው የልማት ቀጠና ለማድረግ ነበር ከ9 ዓመታት በፊት የግጭት ቀድመ ማስጠንቀቂያና አፋጣኝ ምላሽ ሜካኒዝምን ያቋቋሙት፡፡
ሜካኒዝሙ በሀገሪቱ የሚገኘውን የመነገስት መዋቅርና ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ግጭቶች እንዳይከሰቱ ከተሰከቱም በአፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ ሲሰራ ቆይቷል፡፡በኢትዮጵያ የሜካኒዝሙ የካራሞጃና የሶማሊያ ቅርንጫፎች ሜካኒዝሙ ለቀጣዩቹ 9 ዓመታት የሚመራበት አዲስ ስትራቴጂ ለመንደፍ በሀዋሣ ከተማ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ እንደተገለፀውም በሁሉም ሀገራት በአርብቶ አደሩ አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላም እየሰፈነባቸው መጥቷል፡፡
የሜካኒዝሙ ዳይሬክተር ዶክተር ማርቲን ኪማኒ እንዳሉት በሀገሪቱ እስከ ቀበሌ ደረጃ መዋቅሮችን በመዘርጋት ባህላዊና ዘመናዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ድንበር ተሻጋሪ ግጭቶች በከፍተኛ ሁኔታ ለመከላከል ተችሏል፡፡በቀጣናው በተፈጥሮ ሀብት፣ በግጦሽ፣ በውሃ፣በባህላዊ ተፅዕኖና ሌሎች ምክንያቶች አልፎ አልፎ ግጭቶች ሲከሰቱም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አቅም ተፈጥዋል ብለዋል፡፡
አባል ሀገራቱ ግጭቱን ለማስወገድ ፈጣን የመረጀ ልውውጥና የጋራ አፈተት ስልቶች ማዳበራቸውንም ተናግረዋል፡፡ይህም ዘላቂነት ያለው ሰላም ከማምጣቱም ሌላ በሀገሪቱ መሀከል የመተማመንና በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ አበሮ የመስራት ልምድ በመፍጠሩ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑንም ነው ዳይሬክተሩ የገለፁት፡፡
ኢትዮጵያ  ከአባል ሀገራቱ ጋር በመተባበር ሜካኒዝሙን እንዲቋቋም ግንባር ቀደም ሚና ትጫወታለች ያሉት ዶክተር ማርቲን በደቡብ፣ በኦሮሚያ፣ ሶማሌ ክልሎች ድንበር አልፎ አልፎ የሚከሰቱት ተሻጋሪ ግጭቶችን በመከላከል በኩል የበኩሏን እየተወጣች ትገኛለች፡፡
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ምትኩ ካሳ ኢትዮጵያ በአርብቶ አደሩ አካባቢ ከፌደራል እስከ ቀበሌ ቅድመ ማስጠንቀቂያና አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጡ መዋቅሮችን በማደራጀት ዘላቂነት ያለው ሰላም እየስመዘገበች ትገኛለች፡፡ሜካኒዝሙ ይመራበት የነበረው የ5 ዓመታት ስትራቴጂ በቅርቡ አብቅቷል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው አባል ሀገራት ለሚቀጥሉት ዓመታት የሚመራበት አዲስ ስትራቴጂ እንዲነደፍ ባስተላለፉት ውሳኔ መሠረት በሀገራት ደረጀ ለስትራቴጂው ግብአት መፈለጉን ገልፀዋል፡፡
የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተወካይ አቶ አኒሳ መልኮ ስብሰባውን ሲከፍቱ እንዳሉትም ኢትዮጵያ ከካሜካኒዝሙና በየደረጃው ካሉ የአጐራባች ሀገራት የአስተዳደር መዋቅሮች የተጠናከረ ግንኙት በመፍጠb ግጭቶች እየቀነሱ መጥተዋል፡፡ሀገሪቷ ከአጎራባቾች ጋር በመተባበር የጀመረቸው ግጭትን የመከላከልና ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ይበልጥ ዳብሮ ተጠቃሚ እንድትሆን የስብሳው ተሳታፊዎች ለስትራቴጂው ገንቢ የሆኑ ሀሳቦች በመንደፍ የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በስብሰባው ከሜካኒዝሙ፣ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም ከሚመለከታቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር