የሐዋሳ ማራቶን ታቅዷል



.ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ  በሐዋሳ ዓለም አቀፍ ደረጃ ሊኖረው የሚችል የማራቶን ውድድር ለማዘጋጀት ማቀዱ ታወቀ፡፡ የሃዋሣ ከተማ ዓለምአቀፍ ደረጃ ያለው የማራቶን ውድድር ለማዘጋጀት ተስማሚ አየርና የመሮጫ ጐዳና ያላት ሲሆን በ2013 የመጀመሪያ ማራቶንን ለማካሄድ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላይ እየተሯሯጠ ነው፡፡  ባለፈው ሳምንት በሐዋሳ ከእንግሊዝ ሕፃናት አድን ድርጅት ጋር በመተባበር ‹‹ሁሉም›› በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር የተካሄደው በርካታ የውጭ አገር እና የከተማውን ህዝብ በማሳተፍ ነበር፡፡ የውድድሩ አዘጋጆች እንደገለፁት ከ60 በላይ የውጭ አገር ተሳታፊዎች ከዩናይትድ ;;;; ጀርመንና ጣሊያን በመምጣት ተሳትፈዋል፡፡
ባለፈው እሑድ በዋናው የግማሽ ማራቶን ውድድር ላለፉት ሁለት ዓመታት አሸናፊ የነበሩት ኬንያውያን  አልተሳካላቸውም፡፡ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን ታዋቂ አትሌቶች በተሳተፉበት የሴቶች 21 ኪሎ ሜትር የማረሚያ ቤቶቿ አትሌት ዘይቱና አረዋ ርቀቱን 1 ሰዓት 13 ደቂቃ 40 ሰከንድ አጠናቃ ስታሸንፍ፣ ሁለተኛ የማረሚያ ቤቶቿ ጽጌረዳ ግርማ ሦስተኛ ቀነኔ ሆነዋል፡፡ በወንዶች ምድብ የግል ተወዳዳሪው ሀብታሙ አሰፋ 1 ሰዓት 03 ደቂቃ፣ 38 ሰከንድ በማጠናቀቅ አንደኛ ሲወጣ፣ ስንታየሁ መርጋና ፀጋዬ አሰፋ ከኦሮሚያ ፖሊስና በግል ሁለተኛና ሦስተኛ ሆነው የብርና ነሐስ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በሁለቱም ጾታ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ በመውጣት ያጠናቀቁ አትሌቶች የአሥራ አራት፣ የሰባት እና የሦስት ሺሕ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በሌላ በኩል በታዋቂ አትሌቶች መካከል በተደረገው ሰባት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ሴቶች፣ ፀጋ ደሳለኝ ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ ሁለተኛና ሦስተኛ የወጡት ደግሞ ትዕግስት ተካና ሃና አሕመድ ናቸው፡፡ በተመሳሳይ ርቀት ወንዶች የሻሸመኔ አትሌቲክስ ክለብን ወክሎ የተወዳደረው መርዕድ መኮንን አንደኛ ሲወጣ፣ የደቡብ ፖሊሶቹ ደጀኔ ሙላይ እና አብዱሶ ማላ ሁለተኛና  የመጀመሪያ ማራቶንን ለማካሄድ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላይ እየተሯሯጠ ነው፡፡ በሌላ በኩል ቀዋል፡፡ ብዙኀን የተሳተፉበት የሰባት ኪሎ ሜትርና ሁለት ኪሎ ሜትር የሸፈነ የሕፃናት ውድድር ተካሒዷል፡፡በአጠቃላይ ታዋቂ አትሌቶቹን ጨምሮ በዚህ ‹‹ሁሉም›› ዘመቻ ቁጥራቸው እስከ አሥር ሺሕ የሚገመቱ ተወዳዳሪዎች ነበሩ፡፡ በክብር እንግድነት ኃይሌ ገብረ ሥላሴን ጨምሮ የተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ በተመጣጠነ ምግብ ምክንያት የእናቶችና ሕፃናት ሞትን በመከላከል ላይ ትኩረት ያደረጉ መርሆች  በውድድሮቹ ታጅበው ቀርበዋል፡፡
http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_content&view=article&id=2245:2012-05-12-11-00-07&catid=103:2011-01-30-11-15-00&Itemid=501

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር