በሲዳማ ዞን ሐዋሣ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደሮች የሐዋሳ ሐይቅንና ጥልቀት የሌላቸው ጉድጓዶችን በመጠቀም ከ800 በላይ ሄክታር መሬት በአነስተኛ መስኖ አልምተው ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ:


በሲዳማ ዞን ሐዋሣ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደሮች የሐዋሳ ሐይቅንና ጥልቀት የሌላቸው ጉድጓዶችን በመጠቀም ከ800 በላይ ሄክታር መሬት በአነስተኛ መስኖ አልምተው ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ::ተጠቃሚ አርሶ አደሮቹ እንደተናገሩት በአመት 4 ጊዜ የተለያዩ የጓሮ አትክልቶችንና ወቅታዊ ሰብሎችን በማምረት እስከ 1 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘት ችለዋል::
የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ሻሾ እንደገለጹት በመስኖው ልማት ከ2ሺ 500 በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ሆነዋል::በመንግሥት ድጋፍ የተገኙትን 20 የውሃ መሣቢያ ሞተሮችን በ1ለ5 ትስስር ለተደራጁ አርሶ አደሮች በማከፋፈል ዓመቱን በሙሉ ዝናብ ሳይጠብቁ በማምረት ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል::
አርሶ አደሮቹ ቲማቲም፣ ጥቅል ጎመን፣ ሽንኩርትና ቃሪያ ከሚያለሙዋቸው ምርቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል::በአሁኑ ጊዜ ማሳ ላይ ከሚገኘው ምርትም ከ1 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ክፍሌ ገልፀዋል ሲል የሲዳማ ዞን የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ ዘግቧል::

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር