በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ቦንድ መግዛታቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ፡


በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ቦንድ መግዛታቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ለገሰ ላሺ እንደገለፁት በቦንድ ግዥው የተሳተፉት በወረዳው 33 የገጠር ቀበሌያትና 4 ከተሞች የሚኖሩ የተለያዩ የእምነት ተቋማት፣ እድሮች እንዲሁም ሞዴል አርሶ አደሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡
በተለይም የተፈሪ ኬላ ከተማ ነዋሪዎች የ41 ሺህ 45ዐ ብር ቦንድ እጅ በእጅ ክፍያ በመግዛት ቀዳሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የወረዳው ደህኢዴን ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ዘዳግም በበኩላቸው ህብረተሰቡ ከ5ዐ እስከ 1ዐዐዐ ብር ዋጋ ያለውን ቦንድ ግዥ መፈፀሙን ገልፀዋል ሲል የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር