በሲዳማ ዞን ይርጋአለም ከተማ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከስድስት መቶ ሺህ ብር በሚበልጥ ገንዘብ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ቦንድ ለመግዛት ቃል ገቡ፡


በሲዳማ ዞን ይርጋአለም ከተማ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከስድስት መቶ ሺህ ብር በሚበልጥ ገንዘብ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ቦንድ ለመግዛት ቃል ገቡ፡፡ በከተማው በፎቶና ቪዲዮ ስራ የሚተዳደሩት አቶ ናአሚን ፍረሕይወት በበኩላቸው የ5 ሺህ ብር ቦንድ ገዝተው በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከፍለው ለማጠናቀቅ ቃል ገብተዋል፡፡
በሌላም በኩል በሸቀጣሸቀጥ ንግድ ስራ የተሰማሩት ወ/ሮ አበባየሁ ለገሰ የ3 ሺህ ብር ቦንድ የገዙ ሲሆን አምስት መቶ ብር ስጦታ መለገሳቸውንም ገልፀዋል፡፡ የከተማው ከንቲባ አቶ ወንድወሰን ቦልካ ጉዳዩን አስመልክተው እንደገለፁት የግድቡን ስራ ከዳር ለማድረስ የከተማው ህብረተሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት በተለያዩ ጊዜያት ሰፊ የገንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
በየጊዜው በተደረገው ውይይት በከተማው የሚኖሩ ነጋዴዎች፣ የሐይማኖት ተቋማትና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ቦንድ ለመግዛት ቃል መግባታቸውን የገለፁት ከንቲባው በቃላቸው መሰረት ግዥውን በመፈፀም ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ሪፖርተራችን መለሰ ሱኩሌ ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ እንደዘገበው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር