በሀዋሳ ከተማ የሚገኘው በተለምዶ አሞራ ገደል የሚገኘው የፍቅር ሀይቅ በቆሻሻ እየተበከለ ነው



በሀዋሳ ከተማ የሚገኘው በተለምዶ አሞራ ገደል የሚገኘው የፍቅር ሀይቅ በቆሻሻ እየተበላሸ ሲሆን ሀይቁ በፌስታል፤ በጫት ገራባ፤ በብሰኩትና የመስቲካ ማሸጊዎች እየተጣለ ተቖጣጣሪ ባለቤት ያጣ ይመስላል፡፡ዛሬ እሁድ አፕሪል 15/2012 አካባቢውን የጎበኘሁ ሲሆን የመግቢያ ገንዘብ የሚስከፍሉ Sidama Development Association Hawassa Serial No.272892 ካርኒ ለሁለት ሰው 10 ብር የከፈልኩ ሲሆን ለምን በየተራ የተመደቡ ሰዎች ለምን እየተከታተሉ እነደማያፀዱ ጥይቄያቸው እናፀዳዋለን ከማለት በስተቀር የአንድ ቀን ቆሻሻ ስለማይመስል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡እጅግ አሳዛኙ ነገር የከተማው ድሬኔጅ ኔትወርክ ከሐይቁ ጋር ሜያዙ እጅግ አሳፋሪ ስራ አየተሰራ መሆኑን የከተማው አካባቢ ተቆርቋሪዎች እየሞገቱ ሲሆን እስከአሁን ሰሚ ጆሮ ባለመገኘቱ የአካባቢ ተቆርቋሪዎች ድምፃቸውን ሳይሰለቹ በማሰማት ይህችን ውብ ከተማ ከብክለት ሊታደጓት ይገባል እያሉ ነው፡፡
በፎቶግራፉ ላይ የምትመለከቱት ቖሻሻ በአሞራ ገደል የፍቅር ሀይቅ በዚሁ ዕለት የተነሳ ነው፡፡ 

by Melaku Ayele from Hawassa

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር