በሀዋሣ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ መሠረታዊ ማህበራት ከ9 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ማስመዝገብ መቻላቸው ተገለፀ::
በሀዋሣ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ መሠረታዊ ማህበራት ከ9 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ማስመዝገብ መቻላቸው ተገለፀ::የወረዳው የግብይትና ህብረት ስራ ጽህፈት ቤት እንዳለው በ23 ቀበሌያት የተቋቋሙት ማህበራት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማቱን በማገዝ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው::
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጴጥሮስ ማርቆስ ማህበራቱ በሁለገብ መሠረታዊ ህብረት ስራ፣ በወጣት፣ በገንዘብ ቁጠባና ብድር እንዲሁም በወተትና የወተት ተዋፅኦ፣ በኃይድሮ ኤሌክትሪክና ሶላር ማህበራት የተቋቋሙ መሆናቸውን ተናግረዋል::መስኖ፣ ማዕድንና የደን ልማት ቀሪዎቹ ማህበራቱ የተደራጁባቸው መስኮች መሆናቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል::
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መኮንን ወላንሳ በበኩላቸው ህብረት ስራ ማህበራት የነበሩባቸውን የአመለካከትና ግንዛቤ ችግር ቀርፈው ችግር ፈቺ እየሆኑ መምጣታቸውን መናገራቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዘግቧል::
Comments
Post a Comment