በሲዳማ ዞን ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ህጋዊ ነጋዴዎችን በብዛትና በጥራት ማፍራት መቻሉን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ አስታወቀ :


በሲዳማ ዞን ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ህጋዊ ነጋዴዎችን በብዛትና በጥራት ማፍራት መቻሉን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡መምሪያው ከአንድ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነጋዴዎች የንግድ ፈቃድ ሰጥቶ ወደ ስራ ማስማራቱንም ጨምሮ ገልጿል፡፡
በዞኑ 19 ወረዳዎችና 2 የከተማ አስተዳደሮች 1 ሺህ 4 መቶ 44 የንግድ ፈቃድ ምዝገባ ለማካሄድ ታቅዶ ከዕቅድ በላይ 1 ሺህ 6 መቶ 12 የንግድ ምዝገባ ማከናወን መቻሉን በመምሪያ የንግድ ማስፋፊያ ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሲኮራ ኤቢሶ ገልፀዋል፡፡በበጀት አመቱ 1ዐ ሺህ 214 የሚሆኑ የንግድ ተቋሟት የምዝገባና የንግደ ፈቃድ አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልፀው በዚህም 1 ሚሊዮን 52 ሺህ ብር ገቢ መገኘቱን አስረድተዋል፡፡ሪፖርተራችን ካሳ ጀንቦላ ከበንሳ ቅርንጫፋችን እንደዘገበው፡፡፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር