ሀዋሳ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ የመጣውን የወላጅ አጥ ህፃናት ቁጥር ችግር ለመፍታታ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የከተማው ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መምሪያ አስታወቀ፡



ሀዋሳ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ የመጣውን የወላጅ አጥ ህፃናት ቁጥር ችግር ለመፍታታ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የከተማው ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መምሪያ አስታወቀ፡፡መምሪያው ከተለያዩ የዕምነት ተቋማትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሀገሪቱ አዲስ የሆነውን የፎስተር ኬር ኘሮግራም እንደሚጀምርም ገልጿል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መምሪያ በሀገሪቷ በቅርቡ ተግባራዊ መደረግ የተጀመረውን የፎስተር ኬር ኘሮግራም ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡ከቢታኒ ቤተክርስትያን ሰርቪስና ከርሆቦት ዴቨሎኘመንት ኤንድ ሳፓርቲንግ ኦርጋናይዜሽን ጋር በመተባበር ለወንጌላዊያን አብያተክርስትያናት መሪዎች መምሪያው ባዘጋጀው የምክክር ስብሰባ ላይ እንደተባለውም በከተማው የፎስተር ኘሮግራም ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡
የመምሪያው ኃላፊ ወይዘሪት ስምረት ግርማ እንዳሉት ከ4 ወራት በኋላ የሚጀመረው የፎስተር እንክብካቤ በከተማው በህፃናት ማሳደጊያ ተቋማት የሚገኙ ከ2ዐዐ በላይ ህፃናትን ጨምሮ በየደረጃው በጐዳና ላይ ያሉት ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ህፃናት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡በኘሮግራሙ ወላጅ አጥ ህፃናትና ተጋላጭ የሆኑ ቤተሰቦች ድጋፍ ያገኛሉ ያሉት ወይዘሪት ስምረት ወላጅ አጥ ህፃናት የቤተሰብ ፍቅር አግኝተው እንዲያድጉ ከቤተሰቦቻቸው ካልሆነም ፈቃደኛ ከሆኑ ሌሎች ቤተሰቦች እንዲያድጉ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡ ኘሮግራሙ የህፃናትን ችግር ለመፍታት ከሚደረጉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት አንዱ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
ህፃናቱን የሚያሳድጉ ቤተሰቦች በየእምነት ተቋሙ የሚመለመሉ በመሆናቸው የእምነት ተቋማት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የህዝቡ የመተሳሰብና የመተባበር ባህል በማጐልበትና በማሳመን ሞራላዊና መንፈሳዊ ግዴታቸው እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡የቢታኒ ክርስትያን ሰርቪስ የሀገር ውስጥ ተጠሪ አቶ ሲቢሉ ቦጃ በበኩላቸው የፎስተር እንክብካቤ በቅርቡ በአዳማ ከተማ በ1ዐዐ ህፃናት ተጀምሮ ውጤታማ ሆኗል፡፡በአጭር ጊዜ 25 ህፃናት ፈቃደኛ ከሆኑ ሌሎች ቤተሰቦች ተቀላቅለዋል ብለዋል፡፡
በሀዋሣ ከተማም ከመምሪያውና ከሌሎች ሦስት አገር በቀል ተቋማቱ ጋር በመተባበር 3ዐዐ ህፃናትን በመቀበል ኘሮግራሙ ለመጀመር ዝግጅቱ ተጠናቆ የማስተዋወቅ ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር