በሲዳማ ዞን የመጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ እየተካሄደ ነው



አዋሳ, መጋቢት 12 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በሲዳማ ዞን ከ97 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ በጀት በ19 ወረዳዎች የውሃ ተቋማት ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን የዞኑ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ገለጸ።
የመምሪያው ኃላፊ አቶ አብሩ ደቃሞ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በመንግስት፣ በአለም ባንክ፣መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና በህብረተሰቡ ተሳትፎ በ19 ወረዳ በመገንባት ላይ ካሉት የውሃ ተቋማት መካከል ጥልቅ ፣መለስተኛና አነስተኛ ጉድጓድ ምንጭ የማጎልበት ይገኝበታል።
የአዋዳ ቦርቻ ከፍተኛ ምንጭ ግንባታና ማስፋፊያን በማጠናቀቅ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው ለሸበዲኖና ጎርቼ የሚገነቡ ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች የመገንባት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የይርጋለምና አለታ ወንዶ ከተሞች የመጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ለማከናወን ጨረታ ወጥቶ አሸናፊው ግንባታ መጀመሩን ገልጸው ለሁለቱ ከተሞች የመጠጥ ውሃ ግንባታ ከ29 ሚሊዮን ብር በላይ መመደቡን አስታውቀዋል።
በዞኑ የተጀመረው የመጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ ከ60 በመቶ በላይ መጠናቀቁን አስታውቀው በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ህብረተሰቡ በገንዘብ በቁሳቁስና ጉልበት አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቁመው ግንባታቸው ሲጠናቀቅ ከ760 ሺህ የሚበለጥ የዞኑ ነዋሪ ተጠቃሚ በማድረግ የዞኑን የውሃ አቅርቦት ሽፋን ከ41 በመቶ ወደ 60 በመቶ እንደሚያሳድገው ገልጸዋል

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር