በሀዋሣ ዩኒቨርስቲ ከሁሉም የትምህርት ክፍል ለተውጣጡ ተማሪዎች በስነ ተዋልዶ ጤናና ኤች አይቪ ኤድስ መከላከል ዙሪያ ትምህርት ተሰጠ፡፡

New

በሀዋሣ ዩኒቨርስቲ ከሁሉም የትምህርት ክፍል ለተውጣጡ ተማሪዎች በስነ ተዋልዶ ጤናና ኤች አይቪ ኤድስ መከላከል ዙሪያ ትምህርት ተሰጠ፡፡ስልጠናው ጤናማ፣ ብቁና አምራች ዜጋ ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት የሚያግዝ መሆኑም ተገልጿል፡፡የሀዋሣ ዩኒቨርስቲ ኤች አይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት ረዳት ዳሬክተር አቶ አለማየሁ አበበ እንደገለፁት የስነ ተዋልዶ ጤና እና የኤች አይቪ ኤድስ ትምህርት ማግኘታቸው ከነዚህ ጋር ተያይዞ የሚጋረጡ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል ያስችላቸዋል፡፡
ዩኒቨርስቲው ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ዘርፎች አንድ ኤች አይቪ ኤድስና የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች የተማሪዎች ችግር እንዳይሆኑ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡ከሁሉም የትምህርት ዘርፍ የተውጣጡ ተማሪዎች በመገኘታቸውም አላስፈላጊ እርግዝና እና ሌሎች በሽታዎችን ለመከላከል ያገኙትን ትምህርት ለሌሎች ተማሪዎች ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሚያሰችልም ጠቁመዋል፡፡  ይህም ውይይት የመማር ማስተማሩን ሂደት እንዳያስተጓጉል እና ጤናማ፣ ብቁ አምራች ዜጋን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የደቡቡ ክልል ሀገርን እንወቅ የባህል ልማትና ቱሪዝም ፎረም ዋና መስራችና ስራ አስኪያጅ ወጣት አሸናፊ ግዛው እዲህ አይነት ውይይቶች ተማሪዎች በጋራ ማድረጋቸውንና ግልጽ ሆነው የመናገር ባህል እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል ሲል ተናግሯል፡፡በቀጣይም እንደዚህ አይነት ፎረሞችን በክልሉ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች በማዘጋጀት እራስን ባለመጠበቅ የሚመጡ በሽታዎች በዩኒቨርስቲዎች ለመቀነስ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡በሌላ በኩልም ተማሪዎቹ የካምፖስ የፍቅር ሕይወት ጣጣ ወይስ አላማ በሚል ከነባራዊ ሁኔታ መነሳት ተማሪዎቹ በግልጽ ተወያይተዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር