አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአውስትራሊያ ጠቅላይ ገዢ አቀረቡ

New

አዲሰ አበባ, የካቲት 30 ቀን 2004 (አዲስ አበባ) - አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአውስትራሊያ ጠቅላይ ገዢ ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡
ሚኒስቴሩ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቀው አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ለአውስትራሊያ መንግስት ጠቅላይ ገዢ ሚስ ኩዌንቲን ብሪክ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል፡፡
አምባሳደሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት የሁለቱን አገራት ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንዲሚሰሩ በመግለጽ አውስትራሊያ ኢትዮጵያ ለተያያዘችው የልማት እንቀስቃሴ ድጋፍ እንድትሰጥ ጠይቀዋል፡፡
በወቅቱ አውስትራሊያ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር አመርቂ ውይይት መካሔዱንም አስረድተዋል፡፡
ጠቅላይ ገዢዋ ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያን መጎብኝታቸውንና በወቅቱ በአገሪቱ መንግስት ለተደረገላቸው አቀባበልና መስተንግዶ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማእከል በመሆኗ የአውስትራሊያ አፍሪካ ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያን ማእከል አድርጎ እንደሚንቀሳቀስም ጠቁመዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር