የዳዬ በንሳን ጨምሮ በደቡብ ክልል ከ263 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነቡ ስድስት የቴክኒክ ሙያና ትምህርት ስልጠና ኮሌጆች ስራ ጀመሩ

አዋሳ, መጋቢት 20 ቀን 2004 (ሃዋሳ) -
በደቡብ ክልል ከ263 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተጀመሩ ስድስት የቴክኒክ ሙያና ትምህርት ስልጠና ኮሌጆች ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የክልሉ ቴክኒክ መያና ትምህርት ስልጠና ቢሮ ገለጸ፡፡ የኮሌጆቹ መገንባት በክልሉ ያሉት መሰል ኮሌጆች ብዛት ወደ 22 ያሳድገዋል ።
በቢሮው የልማት ዕቅድ ፣ ዝግጅት፣ ክትትልና ግብረ መልስ የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ኢዮብ አዳ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በ2002 ግንባታቸው ተጀምሮ ዘንድሮ የተጠናቀቁት ኮሌጆች በሳውላ ፣ በተርጫ ፣በጂንካ በሃላባ ፣ በወራቤና በዳዬ ከተሞች የሚገኙ ናቸው፡፡
ለኮሌጆቹ የመምህራን ቅጥር በማከናወንና የውስጥ ድርጅት በማሟላት በአሁኑ ወቅት ከ6ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብለው በአጫጭር ፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ የስልጠና ፕሮግራም መጀመራቸውን አመልከተዋል፡፡
ኮሌጁቹ ከሚያሰለጥኑባቸዉ መስኮች መካከል ኮንስትራክሽን ፣ አውቶሞቲቨ ፣ ብረታብረት ፣ ኤሌክትሪክ ሲቲ ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ጨርቃጨርቅና ቆዳ ቴክኖሎጂ እንደሚገኙባቸዉ የስራ ሂደቱ ባለቤት አስረድተዋል፡፡
ተቋማቱ በውስጣችው ቤተ መጻህፍት ፣ ቤተ ሙከራ ፣ የመማሪያ ክፍሎች ፣ ቢሮዎችና ሌሎችም ለመማር ማስተማሩ ስራ የሚያገለግሉ ከ12 እስከ 13 ክፍሎች ማካተታቸወን ጠቁመው የግንባታቸው ወጪ ሙሉ በሙሉ በመንግስት የተሸፈነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የተቋማቱ መገንባት የህብረተሰቡንና የገበያው ፍላጎት መሰረት በማድረግ ውጤታማና የተቀናጀ ስልጠና በመስጠት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ስራላይ የሚሰማሩ ባለሙያዎች በብዛትና በጥራት በማፍራት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ለማሳካት በተለይ ወደ ኢንዱስትሪው መር ልማት ለመሸጋገር ከፍተኛ አስተዋጾኦ አንዳላቸው አሰረድተዋል፡፡
ኮሌጆቹ ሀገሪቱ የምትፈልጋቸው የስራ ዲስፕሊን ያላቸው ፣ በራሳቸው የሚተማመኑና በሙያ ክህሎታቸው የዳበሩ ፣ ስራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆን ስራ ፈጣሪና በስራ ክቡርነት የሚያምኑ ባለሙያዎችን በማፍራት በመካከለኛ ደረጃዎች የሰለጠነ የሰው ሃይል የማፍራት ዓላማ ያነገቡ መሆናቸዉንም ተገልጿል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር