በሲዳማ ዞን በሁሉም ቀበሌያት 2ዐ5 ሺህ 9 መቶ 24 ሄክታር መሬት በተፋሰስ ለማልማት ከታቀደው 75 በመቶ ማከናወን መቻሉን የዞኑ ግብርና ልማት መምሪያ ገለፀ፡፡


በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ በግማሽ የበጀት አመት ቀጥታና ቀጥታ ካልሆኑ የገቢ አርዕስቶች ከ5 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ገቢ መሰብሰቡን የወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ከበደ መኩሪያ እንደገለፁት ገቢው ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ብር ብልጫ እንዳለውና የእቅዱ አፈፃፀም 98 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

ለገቢው መገኘት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ክትትልና የቅርብ ድጋፍ ማድረጋቸው እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤት ጋር በቅንጅት መስራቱ አስተዋጽኦ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡በጽህፈት ቤቱ የገቢ አሰባሰብ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ፍስሐ በኬ በበኩላቸው ለባለሙያዎች በገቢ አሰባሰብ ስርአት የሚሰጠው የግልፀኝነት፣ የተጠያቂነትና የስነ ምግባር ትምህርት ስራቸውን በታማኝነት እንዲሰሩ አድርጓቸዋል ማለታቸውን የዞኑ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር