በደቡብ ክልል ከ17ሺህ ለሚበልጡ ህፃናት የህፃን ለህፃናት ትምህርት ሊሰጥ ነው::በሲዳማ ዞን በዳራ ወረዳ በ2003 የትምህርት ዘመን የህፃን ለህፃን ትምህርት ፕሮግራም በሙከራ ደረጃ ተጀምሮ ውጤታማ መሆኑን ተልጸዋል፡

New

አዋሳ, የካቲት 28 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በደቡብ ክልል ከ17 ሺህ ለሚበልጡ ህፃናት የህፃን ለህፃናት አቀራረብ ዘዴን በመጠቀም የቅድመ መደበኛ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡
በፕሮግራሙ ከስድስተኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ከአምስት ሺህ የሚበልጡ ጎበዝ ተማሪዎች በማስተማሩ ስራ ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡
የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን በመደገፍ የቁጥጥርና ክትትል ስራዎችን ለሚያከናውኑ ርዕሳነ መምህራን ፣ መምህራን፣ ሱፐር ቫይዘሮችና የወላጅ መምህር ህብረት ተወካዮች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የቢሮው መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ተወካይ ወይዘሮ እናኑ ብዙነህ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የቅድመ መደበኛ ትምህርትና ክብካቤ የህፃናትን አካልና አዕምሮ በማዳበር ለመደበኛ ትምህርት ለማዘጋጀትና መሰረት ለመጣል ቁልፍ ድርሻ አለው፡፡
አስተማማኝ ድጋፍና ክብካቤ ያገኙ ህፃናት ለመደበኛ ትምህርት በጥሩ ሁኔታ እንዲዘጋጁ ስለሚያደረጋቸው ወደ መደበኛ ትምህርት ሲገቡ ለየደረጃው የተዘጋጀውን ስርዓተ ትምህርት በቀላሉ መረዳት እንደሚችሉና አጥጋቢ የመማር ብቃት መመዘኛዎችን አሟልተው ወደ ሚቀጥሉት እርከኖች መሸጋገር ይችላሉ ብለዋል፡፡
በክልሉ በሲዳማ ዞን በዳራ ወረዳ በ2003 የትምህርት ዘመን የህፃን ለህፃን ትምህርት ፕሮግራም በሙከራ ደረጃ ተጀምሮ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ በወረዳው የተገኘውን ምርጥ ተሞክሮ በመቀመር ፕሮግራሙን በክልሉ ሁሉም አካባቢ በማስፋፋት እድሜያቸው ከሶስት እስከ ስድስት ዓመት የሆኑ ህፃናትን ተጠቃሚ ለማደረግ እየሰራ መሆኑን ወይዘሮ እናኑ ገልጸው በ2004 በጀት ዓመት በአራት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ ፕሮግራሙን ለማስጀመር ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡
በፕሮግራሙ ከ17 ሺህ የሚበልጡ ህፃናት እንደሚሳተፉ ገልጸው አንድ አመቻች ተማሪ አምሰት ህፃን በመያዝ በቀን ለአንድ ሰዓት በሳምንት ሁለት ቀን ፊደል ቆጠራን ጨምሮ አንድ ህፃን ወደ መደበኛ ትምህርት ቤት ከመምጣቱ በፊት ማወቅ የሚገባውን የትምህርት ይዘቶች በተለያየ አቀራረብ ዘዴ ያስተምራል ብለዋል፡፡
ፕሮግራሙ ስኬታማ እንዲሆን ለአምስት ሺህ አመቻች ተማሪዎች ስለትምህርት አሰጣጥ ሂደት ስልጠና መሰጠቱን ገልጸው የዳራ ወረዳ ተሞክሮም በአካል ተገኝተው መመልከታቸውን አስታውቀዋል፡፡
በሲዳማ ዞን በዳራ ወረዳ ሻመና ጎዶ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርት ተስፋፅዮን ጴጥሮስና ርዕሰ መምህር ተክለሃይማኖት ሾሮታ የህፃን ለህፃን ትምህርት ፕሮግራም ተማሪና አስተማሪው ህፃን በመሆናቸው ሳይፈራሩ በጨዋታ ፣በዘፈን፣ በመዝሙርና ሌሎች አካባቢያዊ በሆኑ የአቀራረብ ዘዴ ስለሚጠቀሙ ለትምህርት ጥራት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት በገጠር አካባቢ ባለመኖሩና ህፃናት ፊደል ቆጠራ ጭምር የሚጀምሩት መደበኛ ትምህርት ቤት ሲገቡ ብቻ መሆኑን ገልጸው በትምህርቱ ጥራት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተጽእኖ እጅግ ከፍተኛ እንደነበር አስታውቃwል።
በአቀራረቡና በማስተማር ስነዘዴው ልዩ የሆነው ፕሮግራም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ ትምህረት ጽህፈት ቤት የመማር ማስተማርና ምዘና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ዮናስ ዮኦላ ፕሮግራሙ በአመቻች ተማሪዎችና በህፃናቱ መካከል ያለው የዕድሜ የተቀራረበ በመሆኑ በጓደኝነት አብረው እንዲጫወቱ ፣እንዲዘፍኑ፣ፍላጎታቸውን ሳይፈሩና ሳይሸማቀቁ ስለሚገልጹ ህፃናቱ በፕሮግራሙ ላይ ከፍተኛ ፍቅር እንዲኖራቸው የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
በዳራ ወረዳ በሙከራ ደረጃ ተጀምሮ የተገኘውን ልምድና ተሞክሮ በመቀመር ከመጋቢት 2004 ጀምሮ ወደ ስራ ለመግባት የአመቻች ተማሪዎች እና ህፃናት ምልመላን ጨምሮ ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡
በቦርቻ ወረዳ ኦልካ ዳንሼ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የወላጅ መምህር ህብረት ሰብሳቢ አቶ ካሳሁን ዶርሲሶ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት በከተማ ብቻ ሲሰጥ በማየት ለበርካታ አመታት በምኞት መቆየታቸውን ገልጸዋል።
አሁን በየደረጃው ያሉ አስፈፃሚ አካላት ለትምህርት ተደራሽነትና ጥራት በሰጡት ልዩ ትኩረት ለዘመናት የውስጣቸው ምኞት የነበረ ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ምላሽ ማግኘቱን ገልጸው በተለይ የህፃን ለህፃን ትምህርት በቋንቋና ባህል የሚገናኙ ህፃናት እርስ በርስ ሲለሚማማሩ የትምህርቱን ጥራት ከታች ጀምሮ ለመፍታት እንደሚያስችል አስታውቀዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር