በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የቻይና ቋንቋ ትምህርት ፕሮግራም ሊጀመር ነው

New

አዋሳ, የካቲት 16 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የቻይና ቋንቋ ትምህርት ፕሮግራም ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የዩኒቨርስቲው ሶሻል ሳይንስና ሂዩማኒቲ ኮሌጅ ዲን ገለጹ፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሚከፈተውን የትምህርት ፕሮግራም ምክንያት በማድረግ በቻይና ኖርዝ ዌስት ኖርማን ዩኒቨርስቲ የተዘጋጀ የቻይና የባህል ትርኢት ትናንት ማምሻውን ተካሄዷል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ በተካሄደው ስነ ስርዓት ላይ የዩኒቨርስቲው የሶሻል ሳይንስና ሂዩማኒቲ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ንጉሴ መሸሻ እንደገለጹት የቻይና ቋንቋ ትምህርት ፕሮግራምን በሚቀጥለው ሳምንት ለመጀመር የሚያስችል በኮሌጁ የቋንቋዎች ጥናት ክፍል ከ600 በላይ ኢትዮጵያን ተማሪዎች ተመዝግበዋል፡፡
ለመማር ማስተማሩ ስራ የሚስፈልጉ መጻህፍትና መምህራንን ጨምሮ አስላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸው አዲስ አበባ ከሚገኘው የቻይና ኮፊሸንስ ኢንሰቲትዩት ጋር ከዚህ ቀደም ሲል ባደረጉት የመግባባያ የጋር ስምምነት መሰረት በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የቻይና ቋንቋ ማዕከል ተከፍቷል ብለዋል፡፡
ቀደም ሲልም አንድ የዩኒቨርስተው የስራ ሃላፊ በቻይና የልምድ ልውውጥና ጉብኝት ማድረጋቸውን ጠቁመው ዩኒቨርሰቲዎች ከዩኒቨርሰቲዎች ጋር የትብብር ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተመሳሳይ የግንኙነት ፕሮግራም እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡
የባህል ቡድኑን በመምራት የቻይናው ኖርዝ ዌስት ኖርማን ዪኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንት መምጣታቸው የትብብር ግንኙነቱን የበለጠ እንደሚያጠናክረው ዶክተር ንጉሴ አስታውቀው ቻይናና ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣በኢኮኖሚ፣ በባህል፣ በዲፕሎማሲና ሌሎችም ዘርፎች ግንኙነታቸው ተጠናክሮ ጥምረት መፍጠራቸውን እንደሚያሳይ ገልጠዋል፡፡
የቻይና ኢኮኖሚ እያደገ በመሄዱ ኢትዮጵያ ግንኙነቷን በማጠናከር በርካታ የቻይና ኩባንያዎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ማድረጓን ገልጸው በሁሉም መስክ ተወዳዳሪ ለመሆን ከእንግሊዘኛ ባሻገር የአለም ቋንቋን ማወቅ ስለሚጠይቅ በቻይና ኩባኒያ ለመስራትም የካፒታልና የኢኮኖሚ አቅም ይፈጥራል ብለዋል፡፡
የሀገሪቱ ተማሪዎች ወደፊት በተለያዩ ሀገራት ስራ የሚያገኙበት ሁኔታ ለመፍጠር ቋንቋውን መማራቸውና ማወቃቸው ከፍተኛ አስተዋጾኦ እንዳለው አብራርተዋል፡፡
የቻይና ኖርዝ ዌስት ኖርማን ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝደንት ሚስተር ሉይ.ይ በበኩላቸው ኢትዮጵያና ቻይና የቆየ ወንድማዊና ታሪካዊ ግንኙነታቸው በልማት መስኮችም ወደላቀ ደረጃ መድረሱን ገልጸዋል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሚጀመረው የቻይና ቋንቋ ትምህርት ፕሮግራም ትስስራቸውን ይበልጥ በማጎልበት የባህልና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነታቸውን ለማሳደግ የሚበረታታ መሆኑ በተደረገላቸው መስተንግዶና አቀባባል መደሰታቸውን አስታውቀዋል፡፡
የቻይና የባህል ቡድን ያቀረባቸውን ትርኢቶች የተመለከቱት የዩኒቨርስቲው ከአንድ ሺህ 500 የሚበልጡ ተማሪዎችና መምህራን መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር